News detail

Image Here

የዘላቂ ልማት ግቦችን ተግባራዊነት ለማጠናከር ባለሙያዎች ተቀናጅተው ሊሰሩ እንደሚገባ ተጠቆመ። መጋቢት 2/2017 (ፕ.ል.ሚ - አዲስ አበባ)

ዛሬ በፕላንና ልማት ሚኒስቴር የዘላቂ የልማት ግቦች የቴክኒካል ኮሚቴ አባላት ጋር በቀጣይ ስራዎች ላይ ተግባራዊነት ዙሪያ የተደረገው ውይይት ጠቃሚ እንደነበር ተገልጿል።

የቴክኒካል ኮሚቴው አባላት ከፌዴራል ሚኒስቴር አስፈፃሚ የመንግስት ተቋማት፣ ከልማት አጋሮች፣ ከሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ከግል ዘርፍ የተውጣጡ ሲሆን የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት በተቀመጠው ፍኖተ ካርታ በተቀናጀ ስትራቴጂ በጋራ መስራት እንደሚገባ ተገልጿል።

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚንስትር ዲኤታ አቶ በረከት ፍስሃፅዮን ውይይቱ በኢትዮጵያ የዘላቂ የልማት ግቦች ሁሉን ባካተተ መንገድና በዘላቂነት ውጤታማ ሆኖ እንዲተገበር በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን ማሳያ መሆኑን አስረድተዋል።

recent News
  • Image Here

    የዘላቂ ልማት ግቦችን ተግባራዊነት ለማጠናከር ባለሙያዎች ተቀናጅተው ሊሰሩ …

    13 March 2026
  • Image Here

    Ethiopia's Economic Transformation Dialogue

    13 March 2026
  • Image Here

    Kazanchis: A New Chapter in Ethiopia’s Urban Transformation

    13 March 2026