Image Here

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ስታትስቲክስ ልማት ፕሮግራም ላይ ከአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (USAID) ጋር ተወያዬ።

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ስታትስቲክስ ልማት ፕሮግራም ላይ ከአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (USAID) ጋር ተወያዬ።
********************
ህዳር 14/3/2016፤ አዲስ አበባ (የፕ.ል.ሚ)
የፕላንና ልማት ሚኒስቴር በዝግጅት ላይ ባለዉ በኢትዮጵያ ስታትስቲክስ ልማት ፕሮግራም ላይ ከአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (USAID) ጋር ተወያዬ። 
በዉይይቱ ኢትዮጵያ የስነ-ህዝብ ጤና ዳሰሳ (EDHS) በዝርዝር ቀርቦም ተመክሮበታል። 
የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ክብር ዶክተር ነመራ ገበየው በውይይቱ መረጃ ለሀገር ጠቃሚ በመሆኑ   የግብርና፣ የቤቶች፣ የስ-ሕዝብና ሌሎች ዘርፎች ላይ ቆጠራዎችን ለማድረግ እና የኢኮኖሚ ተግባራትን ለማዘመን እንደ ዕቀድ ተይዞ በርካታ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን ገልፀዋል።  እንደመነሻም የኢትዮጵያን የስነ ሕዝብ ጤና ዳሰሳ (EDHS) ለማካሄድ ዝግጅት የተጀመረ ሲሆን ይህም ለተለያዩ ሴክተሮችን አጠቃላይ  መረጃ ለማግኘት ይረዳል ብለዋል፡፡
በውይይቱ ሊሰራ የታሰው የኢትዮጵያ የስነ-ህዝብ ጤና ዳሰሳ (EDHS) በማዕከላዊ ስታትስቲክስ አገልግሎት አማካኝነት የዳሰሳ ጥናቱ ዓላማ፣ አስፈላጊነት፣ አወቃቀርና አተገባበር ፣ተሳታፊዎች፣ መረጃ አሰባሰብና ናሙና አወሳሰድ እንዲሁም ግዜና በጀት ቀርቦ ከአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (USAID) የቀረበው የኢትዮጵያ የስነ-ህዝብ ጤና ዳሰሳ (EDHS) አስፈላጊና ተስፋ ሰጭ መሆኑን አስታዉቆ ድጋፉን እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡
የዳሰሳ ጥናቱ በጤና ሚኒስቴር፣ በአጋር ተቋሟት እና ለጋሽ ድርጅቶች እንደሚሸፈን የተገለፀ ሲሆን ሚኒስቴሮች ሴክተር መስሪያ ቤቶችና ለጋሽ ድርጅቶች በተገኙበት በቅርቡ የማስጀመሪያ ፕሮግራም እንደሚኖር ተጠቅሷል፡፡

recent News
  • Image Here

    የፕላንና ልማት ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ስታትስቲክስ ልማት ፕሮግራም ላይ …

    04 April 2026
  • Image Here

    በኢትዮጵያ ምዘና ለመልካም አስተዳደርና አካታች ዘላቂ ልማትን በመሠረታዊ …

    04 April 2026
  • Image Here

    ክብርት ዶ/ር ፍፁም አሰፋ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር …

    04 April 2026