Image Here

የኢትዮጵያ ዘላቂ ልማት ግቦች (SDG) መሪ ኮሚቴ ሶስተኛውን የሀገር አቀፍ የዘላቂ ልማት ግቦች የፍቃደኝነት ግምገማ (VNR) 2025 ረቂቅ ሪፖርት ገመገመ፡፡

የኢትዮጵያ ዘላቂ ልማት ግቦች (SDG) መሪ ኮሚቴ ሶስተኛውን የሀገር አቀፍ የዘላቂ ልማት ግቦች የፍቃደኝነት ግምገማ (VNR) 2025 ረቂቅ ሪፖርት ገመገመ፡፡

=======================================================================

አዲስ አበባ | ግንቦት 19 ቀን 2017 ዓ.ም

የዘላቂ ልማት ግቦች (SDG) ስትሪንግ ኮሚቴ በፕላንና ልማት ሚኒስቴር የኢትዮጵያን ሶስተኛውን ሀገር አቀፍ የዘላቂ ልማት ግቦች የፍቃደኝነት ግምገማ (VNR) 2025 ረቂቅ ሪፖርት ለመገምገም ሁለተኛውን ስብሰባውን አካሂዷል።

ስብሰባውን በፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ፍጹም አሰፋ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ረዳት ዋና ፀሐፊ እንዲሁም በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ተጠሪና የሰብአዊ ድጋፍ አስተባባሪ በሆኑት በዶ/ር ራሚዝ አላክባሮቭ በጋራ መርተውታል። በምክክር መድረኩም ሀገር አቀፍ የዘላቂ ልማት ግቦች የፍቃደኝነት ግምገማ (VNR) 2025 ረቂቅ ሪፖርት ቀርቦ በኮሚቴው ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል። ይህ ወሳኝ የምክክር ስብሰባ ትላንት ግንቦት 18 ቀን 2017 ዓ.ም በፕላንና ልማት ሚኒስቴር የተካሄደውን የቴክኒክ ኮሚቴ ዝግጅት ስብሰባን ተከትሎ የተካሄደ ነው።

ኮሚቴው ቀጣይ የሚካሄዱትን የምክክር መድረኮች ኢትዮጵያ በሐምሌ ወር 2025 በሚካሄደው ከፍተኛ ደረጃ የፖለቲካ መድረክ ላይ የሚቀርበውን ሰነድ ለማዳበርና ለማጠናቀቅ እጅግ በጣም ጠቃሚ መሆናቸው በውይይቱ አንስቷል። የፈቃደኝነት ግምገማ ሪፖርት ዝግጅቱ ኢትዮጵያ ዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው።

recent News
  • Image Here

    የኢትዮጵያ ዘላቂ ልማት ግቦች (SDG) መሪ ኮሚቴ ሶስተኛውን …

    04 April 2026
  • Image Here

    ኢትዮጵያ ከዩኒሴፍ ጋር በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ያላትን …

    04 April 2026
  • Image Here

    የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ለመቋቋም ያለመ አህጉር …

    04 April 2026