ክብርት የፕላንና ልማት ሚንስትር ዶ/ር ፍጹም አሰፋ የአየር ንብረት ለውጥ በርካታ ኢትዮጵያውያን እያፈናቀለና ለስደት እየዳረገ በመሆኑ ሁሉም ሀገራት ችግሩን ከምንጩ ለማስቀረት ሊተባበሩ እንደሚገባ ዛሬ በናይሮቢ ኬኒያ በተጀመረው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ አሳሰቡ፡፡
****************************************
ነሃሴ12 ቀን 2015 ዓ.ም ናይሮቢ፣ ኬኒያ፤(የፕ.ል.ሚ)
ክብርት የፕላንና ልማት ሚንስትር ዶ/ር ፍጹም አሰፋ እየተሳተፉ የሚገኙበት ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ህብረት አዘጋጅነት በኬኒያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ዛሬ በናይሮቢ ኬኒያ ተጀመረ፡፡
በጉባኤው የመጀመሪያ ቀን ውሎ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ፍጹም አሰፋ በተለያዩ አራት የተለያዩ የሚንስትሮች የፓናል ውይይቶች ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ፕላንና ትግበራ ዙሪያ የሀገራችንን የካበተ ልምድና በሂደቱ የገጠሙ ፈተናዎችንና የመፍትሔ አቅጣጫዎችን የሚያቀርቡ ይሆናል፡፡
ክብርት ሚንስትሯ በመጀመሪያው የፓናል ውይይታቸው የአየር ንብረት ለውጥ በኢትዮጵያ እያደረሰ ያለውን ከፍተኛ ጉዳት ላለፉት አምስት ዓመታት ያጋጠመውን ከፍተኛ ድርቅ በምሳሌነት በማንሳት ያራ ሲሆን በኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው አጀንዳ መሆኑን በመግለጽ ሁሉም ሃገራት ከዚህ ተያይዞ በሚከሰተው ስደት የስደት ተቀባይ ሃገራት የስደት ፖሊሳቸውን እንዲያላሉ እና ስደተኞች ህይወታቸውን በአግባ እንዲመሩ እንዲያደርጉ ጥሪ አድርገዋል፡፡
ክብርት ሚንሰትሯ በኢትዮጵያ በኩል የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ከፍተኛ ተጽእኖና መፈናቀል ብሎም ስደት ለማስቀረት በቁርጠኝነት እየሰራች መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የአረንጓዴ አሻራ ተነሳሽነትንና ስኬትን በማብራራትም ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖን ለመቋቋም እና ስደትን ለማስቀረት በከፍተኛ ቁርጠኝነት እየሰራች መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ይህ ተግባር ሀገራችን ለቀጠናው ሀገራትና ለዓለም እያበረከተች ያለ በረከት መሆኑን አብራርተዋል፡፡
የፓናል ውይይቱ ለአጋር አካላትና ሌሎች አካላት የትግበራ ድጋፍ ጥሪ የቀረበበት መድረክ ሲሆን በዚህ የካምፓላ የአየር ንብረት ለውጥ እና ስደት እወጃ ተነሳሽነት ሁሉም የአፍሪካ ሀገራት እንዲቀላቀሉ እና አጋር አካላት ድጋፋቸውን እንዲያረጋግጡ ጥሪ የቀረበበት ነው፡፡
ክብርት ዶ/ር ፍጹም ለሚመለከተው ሁሉ የአየር ንብረት ለውጥ ተባብሮ የመስራት ጉዳይን የሁሉም ሃገራት ጉዳይ መሆኑን ገልጸው ሁሉም ሀገራትና ድርጅቶች በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚመጣውን ስደት ሁሉንም የሚነካ እንደመሆኑ ከምንጩ ለማስቀረት ለአየር ንብረት ለውጥ ትግበራ የሚያግዝ የገንዘብ እና ሌሎች አማራጮች መተባበር የግድ እንደሚላቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ እ.አ.አ. ከሴፕቴምበር 4 እስከ 6/ 2023 የሚካሄድ ይሆናል፡፡