Image Here

በኢፌዴሪ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር በባለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግበት የነበረውን የክልል የኢኮኖሚ አካውንት የአዘገጃጄት፣የአመራርና የአሠራር መመሪያ/Hand Book/ ይፋ አደረገ። መመሪያው ክልላዊ ኢኮኖሚን በመለካት ከብሔራዊ ኢኮኖሚ አካውንት ጋር የተናበበ ለማድረግ ያስችላል ።

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የክልል የኢኮኖሚ አካውንት መመሪያን የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮችና የሁሉም ክልሎች ፕላንና ልማት ቢሮ ሃላፊዎች እንዲሁም ከፌዴሬሽንና ከህዝብ ተወካዮች ም/ቤት እንዲሁም ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እና ሌሎቾም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ዛሬ በቢሾፍቱ ከተማ ይፋ አድርጓል።

 

በመርሀ ግብሩ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር አቶ በረከት ፍስሃጺዎን ተገኝተው በመክፈቻ ንግግር የከፈቱ ሲሆን በኢትዮጵያ ብሔራዊ የኢኮኖሚ አካውንት ተግባራዊ መሆን የጀመረው በ1953 ዓ.ም መሆኑን ገልጸው፤ ነገር ግን እስካሁን ድረስ ወጥነት ያለው ክልላዊ የኢኮኖሚ አካውንት መመሪያ እንዳልነበር ገልጸዋል።

ከዚህ በፊት ከተማ አስተዳደሮችና ሁሉም ክልሎች ያላቸውን ሐብትና የእድገታቸውን መጠን የሚለኩት ወጥነት በሌለው እና ከብሔራዊ ኢኮኖሚ አካውንት ጋር ባልተናበበ ሁኔታ እንደነበር አውስተዋል።

ይህም ከትክክለኛ መረጃ ላይ ተመስርቶ ኢኮኖሚያዊ ውሳኔዎችን ለመስጠት አዳጋች አድረጎት መቆየቱን ተናግረዋል።

ሚኒስቴርሩ ይህን መነሻ በማድረግ ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ ከከተማ አስተዳደሮችና ሁሉም የክልሎች ፕላንና ልማት ቢሮዎች እንዲሁም ከአጋር አካላት ጋር በመሆን የክልል የኢኮኖሚ አካውንት የአሰራር ዘዴ መመሪያን ሲያዘጋጅ መቆየቱን በንግግራቸው ገልጸዋል። ይህም

የክልል የኢኮኖሚ አካውንት አጠቃላይ ክልላዊ ምርትን ለመለካት የሚያገለግል መሳሪያ ነው ብለዋል።

መመሪያውን ማዘጋጀት ያስፈለገው ከብሔራዊ ኢኮኖሚ አካውንት ጋር የተናበበ እና ወጥ ያለው ክልላዊ የኢኮኖሚ አካውንት እንዲኖር ለማድረግ መሆኑን ተናግረዋል።

በተጨማሪም መመሪያው የክልሎችን የኢኮኖሚ ባህሪ ለመከታተል እና እርምጃዎችን ለመውሰድ ትክክለኛ የመረጃ ምንጪ ሆኖ እንደሚያገለግልም አመላከተዋል።

መመሪያው አለም አቀፍ ደረጃውን በአሟላ መልኩ መዘጋጀቱን ገልጸው፤ ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲዎችን ለማውጣትና ውሳኔዎችን ለመወሰን የሚያስችል የመረጃ ምንጭ እንደሚያገለግልም ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር በከር ሻሌ (ዶ/ር) በበኩላቸው የክልል የኢኮኖሚ አካውንት ለተቀናጀ ሀገራዊ የመረጃ ስርዓት ሚናው የጎላ መሆኑን በማውሳት የመመሪያው ይፋ መሆን ክልሎች ያላቸውን ሐብት በአግባቡ እንዲያውቅ ከማድረግ ባሻገር፤ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ለመንግስት ትክክለኛ የአጠቃላይ አገራዊ ምርት (GDP) መረጃ ለማቅረብ የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡

በመሆኑም አገልግሎቱ የክልል ኢኮኖሚ አካውንት መመሪያ ተግባራዊ ሆኖ የታለመለትን ውጤት እንዲያመጣ የሙያ እና ሌሎች ድጋፎችን ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል። በፕላንና ልማት ማኒስቴር የብሔራዊ አካውንትና የስታትስቲክስ ዋና ሥራ አስፈጻም የሆኑት አቶ ፈለቀ ደምስስ የመመሪያ ሰነዱን አስፈላጊነት ፣የአለም ተሞክሮ ፣ የአዘገጃጀት ሂደት ፣ ያጋጠሙ የችግሮችንና መፍትሄዎችን በጥልቀት በመዳስ ለተሳታፊዎች ለውይይት የቀረበው ሲሆን ከተሳታፊዎች ጥያቄዎችና አስተያየቶች በስፋት ተንሸራሽሮበታል ። ከከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችም መልስና አቅጣጫ ተሰጥቶ ለተግባራዊነቱም በጋራ መግባባት ተጠናቋል ።

መመሪያውን ሙሉ ለሙሉ ለመተግበር ከፌደራል መንግስት ድጋፍ እና ክትትል ሊደረግላቸው እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

recent News
  • Image Here

    በኢፌዴሪ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር በባለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት …

    04 April 2026
  • Image Here

    ኢትዮጵያ በኮፕ28 የአረንጓዴ አሻራና ሌሎች ተሞክሮዎቿን ታካፍላለች - …

    04 April 2026
  • Image Here

    የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ(ዶ/ር) እና የግሎባል ግሪን …

    04 April 2026