ኢትዮጵያ በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ፣ዱባይ በሚካሄደው የCOP28 ጉባኤ ለመሳተፍ በዝግጅት ላይ ነች፡፡
******************************************************************************
አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2015 (የፕ.ል.ሚ)
ኢትዮጲያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፍ (UNFCCC) 28ኛው ጉባኤ (COP28) በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ፣ዱባይ በሚካሄደው ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ በዝግጅት ላይ ነች።
የኢትዮጵያ መንግስት ለ (COP28) የሀገሪቱን ዝግጅት የሚያስተባብር ከፍተኛ ብሄራዊ ኮሚቴ አቋቁሟል። ኮሚቴው በፕላን እና ልማት ሚኒስቴር የሚመራ ሲሆን የሚመለከታቸው የመንግስት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ ኤጀንሲዎች እና የሲቪል ማህበራት ተወካዮችን ያካተተ ነዉ።
የኢትዮጵያ መንግስት በአለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ግንባር ቀደም ሚና ለመጫወት ቁርጠኛ ነው። ሀገሪቱ የበካይ ጋዝ ልቀትን ለመቀነስ እና የታዳሽ ሃይል አጠቃቀምን ለማሳደግ ትልቅ ግቦችን አስቀምጣለች። ኢትዮጵያ በአገሪቷ እየተስተዋሉ ያሉትን የአየር ንብረት ለውጥ ተፅእኖዎች የመቋቋም አቅምን ለመገንባትም እየሰራች ነው።
በ COP28 መድረክ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቅረፍ የወሰደቻቸውን መፍትሔዎች እንደ ልምድ ታካፍላለች ከሌሎች ልምድ ልውውጥ ታደርጋለች ተብሎ ይጠበቃል። ሀገሪቱ የአየር ንብረት ለውጥ ግቦቿን ተግባራዊ ለማድረግ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍም በመድረኩ ታፈላልጋለች።
ኢትዮጵያ በ COP28 ተሳትፎዋ ሀገሪቱ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ መከላከል ያላትን እድገት የምታሳይበት እና የአለም አቀፍ ማህበረሰብ ድጋፍ እንድታገኝ የምትመክርበት እድል ነው። የኢትዮጵያ መንግስት በአለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ውስጥ የመሪነት ሚናውን ለመጫወት ቁርጠኛ ሲሆን በCOP28 ሀገሪቱ ድምጿን እንድታሰማ ትልቅ እድል ይሆናል።