በፕላንና ልማት ሚኒስቴር ከሰኔ 9 እስከ ሰኔ 11 2017 በአዲስ አበባ ለሚከበረው የአፍሪካ የኢቫሊዮሽን ማህበር (AfrEA) 25ተኛ ዓመት የምስረታ በዓል አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ፡፡
=================================================================
አዲስ አበባ | ሰኔ 5/2017 ዓ.ም - (ፕ.ል.ማ)
በፕላንና ልማት ሚኒስቴር ከሰኔ 9 እስከ ሰኔ 11 2017 በአዲስ አበባ ለሚከበረው የአፍሪካ የኢቫሊዮሽን ማህበር (AfrEA) 25ተኛ ዓመት የምስረታ በዓል አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ፡፡
የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ጥሩማር አባተ ከአፍሪካ የኢቫሊዮሽን ማህበር (AfrEA) ፕሬዚዳንትና ከአትዮጵያ የኢቫሊዮሽን ማህበር (EEvA) ጋር በጋራ በመሆን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በዝግጅቱ ከ300 በላይ የውጭ ሀገር ተሳታፊዎችን ጨምሮ የመንግስታት መሪዎች፣ ገምጋሚዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች እና የልማት ባለሞያዎች የሚገኙ ሲሆን በአፍሪካ በክትትልና ግምገማ ትራንስፎርሜሽን ያለውን ለውጥ በሚያተኩር ጉዳይ ላይ ምክክር ይደረጋል ብለዋል፡፡
የአፍሪካ የኢቫሊዮሽን ማህበር (AfrEA) እዩቤልዮ በዓሉ ከኢፌዲሪ ፕላንና ልማት ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የኢቫሊዮሽን ማህበር እና ከሌሎች ዋናዋና ባለድርሻ አካላት ጋር በጥምረት እንደተዘጋጀ ለማወቅ ተችሏል፡፡
የምስረታ በዓሉ “የ25 ዓመታት የልህቀት ጉዞ በአፍሪካ ስር-ተኮር ግምገማ: ጠንካራ የወደፊት አብሮነት መገንባት” በሚል መሪ ቃል ይከበራል ተብሏል፡፡
ማህበሩ በየሁለት ዓመቱ በሚያደርጋቸው ኮንፈረንሶች አፍሪካን መሰረት ያደረጉ የአሰራር ዘዴዎች ዕውቅናና ዋጋ እንዲኖራቸው በማድረግ፤ ዓለማቀፋዊ የግምገማ ስኬቶችን ለመቅረፅ ለአፍሪካ ድምፆች እንዲኖሩ ያደረገ እንደሆነ ተገልፃል፡፡
ኮንፍረንሱ ከሰኔ 9 እስከ ሰኔ 11 2017 ዓ.ም በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን የመሰብሰቢያ አዳራሽ የሚጀረግ መሆኑ ታውቋል።