Image Here

5ኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ውይይት (5th Africa Climate Talks) አዲስ አበባ በሚገኘው በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ቅጥር ግቢ ውስጥ በአፍሪካ የአየር ንብረት ፖሊሲ ማዕከል እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት ተጀመረ።

5ኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ውይይት (5th Africa Climate Talks) አዲስ አበባ በሚገኘው በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ቅጥር ግቢ ውስጥ በአፍሪካ የአየር ንብረት ፖሊሲ ማዕከል እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት ተጀመረ።

ክቡር የፕላንና ልማት ሚንስትር ዴኤታ አቶ ስዩም መኮንን 5ኛውን የአፍሪካ የአየር ንብረት ውይይትን በይፋ ከፍተው አስጀምረዋል።

**********************************************************************************************************

ሚያዚያ 13/2016፤ አዲስ አበባ

ክቡር የፕላንና ልማት ሚንስትር ዴኤታ አቶ ስዩም መኮንን የውይይት መድረኩን በይፋ በከፈቱበት ወቅት እንደገለጹት ስለአየር ንብረት ለውጥ ማውራት ከጀመርን ከ28 ዓመታት በላይ ያለፉ ቢሆንም ዓለም አሁንም በአየር ንብረት ለውጥ ችግር በእጅጉ እየተፈተነች መሆኑን አንስተዋል። በተለይ ኢትዮጵያ ብሎም አፍሪካ በአየር ንብረት እራሳቸው ባልፈጠሩት ችግር እየተገረፉ መሆኑን በማብራራት ዓለም የአፍሪካን ጉዳይ በልዩ ሁኔታ እንዲመለከተውና እውቅና እንዲሰጠው ጠይቀዋል።

አያይዘውም ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ትግበራ በመሪ ደረጃ እንደምትገኝ የገለጹ ሲሆን በሀገር አቀፍ እና በአህጉር አቀፍ ደረጃ እያከናወነች ያለውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን በምሳሌነት በማንሳት በሀገር አቀፍ ደረጃ ባለፉት አምስት ዓመታት ያሳካቸውን የ32.5 ቢሊዮን ችግኞች ተከላና እስከ ጎረቤት ሀገሮች የዘለቀውን የማስፋፋት ስራ በሚመለከት በማብራራት ነው። ሀገራችን ወደሁሉም የአፍሪካ ሀገራት ለማስፋፋት ያላትን ፍላጎት ጠቁመዋል። በሌላ በኩል ሀገራችን የአፍሪካ የአካባቢ ሚንስትሮች ጉባኤ ፕሬዝዳንት እንደመሆኗ የአህጉሪቱን የአካባቢ ሚንስትሮች በመከል ለዘርፈ ብዙ የአካባቢ ተግባራት ያላቸውን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጠዋል።

ክቡር ሚንስትሩ ሀገራችን በእርግጥም በዓለም አቀፍ ውይይት እየተደረጉ ያሉ ውይይቶችን እና የድርድር ስምምነቶችን በተግባር እየፈጸመች ያለች መሆኑኗን በማወጅ በታዳሽ ኢነርጂ ማምረትና በደን ላይ የተመሰረተውን የኢትዮጵያን የኢነርጂ ምንጭ ወደ ሌሎች ታዳሽ የኢነርጂ አመራጮች በፍትሃዊነት መሸጋገር ያለውን ጥረት እና አስፈላጊነት የታላቁን የህዳሴ ግድብ በመግለጽ አስረድተዋል። ሌሎች ሁሉም ሀገራት በትብብርና የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

ከዚህ ባሻገር ሀገራችን ኢትዮጵያ ከሌሎች የተባበሩት መንግስታት አባል ሀገራት በተለየ መልኩ በኢትዮጵያ እ.አ.አ. ከ2011 እስከ 2019 ባለው ጊዜ ያከናወነችውን ሀገራዊ የአየር ንብረት ለውጥ የትግበራ አፈጻጻም ዱባይ ከተካሄደው 28ኛው የተባበሩት መንግስታት ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ የአፈጻጻም ግምገማ በፊት ማካሄዷን ገልጸው የተሰራው ጥናት እንደሚያመለክተውም ሀገራችን ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ሚቲጌሽንና አዳፕቴሽን በርካታ ተግባራት መከናወኑን ያሳየ ከመሆኑም በላይ በአጠቃላይ 82 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚሆን የሚበልጠው በመንግስት ኢንቨስትመንት በአየር ንብረት ለውጥ ላይ መዋሉን አሳይተዋል ብሏል። ይህም የኢትዮጵያን መንግስት በአየር ንብረት ለውጥ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል። ይሁንና ክቡር ሚንስትር ዴኤታ አቶ ስዩም መኮንን እንዳሉት ይህ ፈንድ ከሚያስፈልገው መጠን አንጻር በጣም ዝቅተኛ መሆኑንን ገልጸው ያደጉ ሀገራት በሀገራችን ለተቀረጹ የአየር ንብረት ለውጥ ስትራቴጂዎችና እቅዶች በቂ ፈንድ ማቅረብ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በመጨረሻም ክቡር ሚኒስትሩ ተሳታፊዎች በሚኖራቸው ትርፍ ጊዜ አዲስ አበባ የሚገኙ የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየምን ጨምሮ ሌሎች ከስብሰባ አዳራሹ በቅርብ ርቀት የሚገኙ ፓርኮችን እንዲጎበኙ ጋብዘዋል።

recent News
  • Image Here

    5ኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ውይይት (5th Africa Climate …

    04 April 2026
  • Image Here

    ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ምላሽ ለመስጠት ተግባራዊ …

    04 April 2026
  • Image Here

    04 April 2026