የእርስ በእርስ መገማገሙ ሀገራት በሀጉር ደረጃ የተቀረጸውን የ2063 አጀንዳ አፈጻጸም ሪፖርት የሚቀርብበት በመሆኑ እና ኢትዮጵያም የአጃንዳ 2063 እና የዘላቂ ልማት ግቦችን በልማት ዕቅዶችና ፕሮግራሞች ውስጥ አካታ እየተገበረች ያለች እና የአፈጻጸም ሪፖርቶችንም በየጊዜው እየቀረበች በመሆኑ ክብርት ዶ.ር ፍጹም አሰፋ የግምገማ ስልቱ የኢትዮጵያ ተወካይ ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ።
የአፍሪካ የአቻ ግምገማ ስልት የተወካዮች ኮሚቴ በተለያየ ጊዜ በአካልና በቨርቹዋል የሚካሄድ ሲሆን 39ኛው የአፍሪካ የአቻ ግምገማ ስልት የተወካዮች ኮሚቴ ስብሰባ ክብርት ዶ.ር ፍጹም አሰፋ በተገኙበት ጥር 29/2017 ዓ.ም በቨርቹዋል ተካሂዷል። በዚህ ስበሰባ ላይ የተለያዩ አጀንዳዎች ቀርበው ውይይት የተደረገወባቸው ሲሆን

ክብርት ዶ.ር ፍጹም አሰፋ በቀረቡ አጀንዳዎች ላይ ሀሳባቸውን ሲያቀርቡ የኢትዮጵያ ተወካይ ሆነው ለመጀመሪያ ጊዜ በስብሰባው እንደተገኙና በዚህም ደስተኛ እንደሆኑ በመግለጽ እና አምባሳደር ማሪ-አንቶይኔት ሮዝ-ኳተር የAPRM የመጀመሪያዋ ሴት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው በመሾማቸው እና በዓመቱ ላከናወኗቸው የላቀ ሥራዎች እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ንግግራቸውን ጀምረዋል።
በመቀጠልም በአህጉራችን ውስጥ መልካም አስተዳደርን፣ የህግ የበላይነትን እና የሰብአዊ መብቶችን ለማስከበር APRM እየተጫወተ ያለውን ወሳኝ ሚና ኢትዮጵያ እንምትገነዘብ ገልጸዋል። በተጨማሪም አህጉራችን ቅድሚያ ከምትሰጣቸው ጉዳዮች ጋር እንዲጣጣም ተደርጎ የተዘጋጀውን ከ2025-2028 አዲስ ስትራቴጂክ ዕቅድን ኢትዮጵያ በደስታ የምትቀበለው መሆኑን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብት አስተዳደር በሚል መሪ ቃል የ2025 የአፍሪካ አስተዳደር ሪፖርት ዝግጅትን (በመሬት ሀብት አስተዳደር፣ በማዕድን ሀብት አስተዳደር እና በባህር ሀብት አስተዳደር ላይ ትኩረት የሚያደርግ) ትልቅ ቦታ እንደምትሰጠው ገልጠው አፍሪካ የተፈጥሮ ሀብቶቿን ለማልማትና ለመጠቀም ያለውን ተቀሜታ ገልጸዋል።