Image Here

የግብርና ዘርፍ በአስር ዓመቱ የልማት ዕቅድ የመጀመሪያዎቹ 3 ዓመታት (2013-2015) በዋና ዋና ተግባራት ከዕቅድ በላይ ዕድገት ማስመዝገቡን የፕላንና ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የግብርና ዘርፍ በአስር ዓመቱ የልማት ዕቅድ የመጀመሪያዎቹ 3 ዓመታት (2013-2015) በዋና ዋና ተግባራት ከዕቅድ በላይ ዕድገት ማስመዝገቡን የፕላንና ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ።

***********************************************************************************

መስከረም 9/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ (የፕ.ል.ሚ)

የአስር ዓመት ዕቅድ የመጀመሪያዎቹ 3 ዓመታት (2013-2015) ዋና ዋና አፈጻጸሞች የግብርናው ዘርፍ ከዕቅድ በላይ ዕድገት ማስመዝገቡን ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር የወጣው ሪፖርት ያመለክታል፡፡ በሪፖርቱ የግብርና ዘርፍ ዕድገት በ2013 ከነበረበት 5.1% በ2014 ወደ 5.8% ያደገ ሲሆን በ2015 ደግሞ 6̄.3 በመቶ እድገት አስመዝግቧል፡፡

ዘርፉ በስሩ ካሉት ንዑስ ዘርፎች መካከል ግብርናውን ለማሳደግ ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዘው የሰብል ምርት ሲሆን ለዘርፉ ማደግ 65.5% አስተዋፆ አበርክቷል፡፡ እንዲሁም ደን 8.6% እና እንሰሳት 25.9% ድርሻ እንደነበራቸው በሪፖርቱ ማየት ይቻላል፡፡

በ2015 ዓ.ም ጠቅላላ የሰብል ምርት 627 ሚሊዮን ኩንታል ለማምረት ታቅዶ 639 ሚሊየን ኩንታል ምርት ማግኘት ተችሏል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞም በዘር የተሸፈነ መሬትን በተመለከተ የአነስተኛ አርሶ አደሮች በመኸር በአዝርዕት የተሸፈነ መሬት በ2012 ከነበረበት 13 ሚሊየን ሄክታር በ2015 ወደ 14.06 ሚሊየን ሄክታር ያደገ ሲሆን ይሄም በትላልቅ ኢንቨስትመንት በአዝርዕት ሰብል የተሸፈነ መሬት ብዙ ለውጥ ባላማምጣቱ ምክንያት ምርትና ምርታማነት ለጨመረው በዋናነት መሬትን ከማስፋት ይልቅ ምርታማነት ላይ ትኩረት በመደረጉ ነው።

May be an image of text

በመስኖ የስንዴ ምርትን ከ2013 ከነበረበት 0.6 ሚሊየን ኩንታል በ2015 ወደ 47 ሚሊዮን ኩንታል ማሳደግ ተችሏል ።

በግብርና ዘርፍ በእንስሳት ምርት አፈጻጸም ባለፍት 2 አመታት የእንስሳት ልማት ንዑስ ዘርፍ በአማካይ በ8.4% ያደገ ሲሆን ከ10 ዓመቱ ዕቅድ አንፃር በ0.8% ብልጫ አለው።

የመኸር ወቅት በአነስተኛ አርሶ አደሮች የአዝርዕት ምርት እና በአነስተኛ አርሶ አደሮች እና በሰፋፊ እርሻ በመስኖ የተመሰረተ አዝርት ፣የአትክልት ፣ፍራፍሬና ስራስር ምርት ከፍተኛ የዕድገት ሽግግር የታየባቸው ዘርፎች ናቸው፡፡

የግብርናው ዘርፍ ምርቱን ለገበያ ለማቅረብ ሌላው ቁልፍ ገጽታ የምርቶቹን ትክክለኛ ዋጋ የማግኘት ችግርን ከመፍታት ባለፈ ለዋጋ መረጋጋት ትልቅ ሚና ይጫወታል። ከዚህ አንፃር በእቅድ ዘመኑ ታሳቢ የተደረገ የግብርና ምርቶች የገበያ ትስስር ለመፍጠር በጊዜው ለ35 ሚሊዮን ኩንታል እህል የገበያ እድል ለመፍጠር ታቅዶ የነበረ ሲሆን አፈጻጸሙም 24.4 ሚሊዮን ኩንታል (70%) ነው። በተመሳሳይ 14 ሚሊዮን ኩንታል የአትክልትና ፍራፍሬ ምርት ለገበያ ለማቅረብ ታቅዶ 9.6 ሚሊዮን ኩንታል (የእቅዱ 68%) ለማቅረብ ተችሏል።

በአረንጓዴ አሻራ ፥ በሌማት ትሩፋት ፥ በከተማ ግብርናና በአትክልትና ፍራፍሬም ከፍተኛ ለአለም ተሞክሮ የሚሆኑ አፈጻጸሞች መመዝገባቸዉን ተነተነዉ ሪፖርቱ ይህም በቀጣይ የመካከለኛ ዘመን ተጠናክሮ የሚቀጥል እንደሚሆን ተመላክቷል።

recent News
  • Image Here

    የግብርና ዘርፍ በአስር ዓመቱ የልማት ዕቅድ የመጀመሪያዎቹ 3 …

    04 April 2026
  • Image Here

    የፕላንና ልማት ሚኒሰቴር የ2015 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም …

    04 April 2026
  • Image Here

    19ኛው የአፍሪካ የአካባቢ ሚኒስትሮች መደበኛ ጉባኤ አዲስ አበባ …

    04 April 2026