Image Here

ኢትዮጵያ በ28ኛ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ለመሳትፍ ዝግጅቷን ማጠናቀቋን የፕላንና ልማት ሚኒስቴር አሰታወቀ።

ኢትዮጵያ በ28ኛ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ለመሳትፍ ዝግጅቷን ማጠናቀቋን የፕላንና ልማት ሚኒስቴር አሰታወቀ። 

 በ28ተኛው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
***************************************************************************************************
ህዳር/12/2016 ፤ አዲስ አበባ (የፕ.ል.ሚ)
የፕላንና ልማት ሚኒስቴር  እአአ ከህዳር 30 እስከ ታህሳስ12 በተባባሩት አረብ ኤምሬትስ በዱባይ የሚካሄደውን 28ተኛ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
ጋዜጣዊ መግለጫውን የሰጡት የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ክብር ዶክተር ነመራ ገበየው ኢትዮጵያ በዱባይ፤ አረብ ኤምሬትስ በሚካሄደው 28ተኛው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ከፍተኛ ዝግጅት ማድረጓን የገለፁ ሲሆን ያላትን አቋም ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ የምታሳውቅበት መድረክ እንደሚሆንም ጠቁመዋል። ጉባኤው በሶስት ምዕራፎች ተከፍሎ የተለያዩ ክንውኖች እንደሚኖሩትም ገልፀዋል፡፡
በጉባኤው የመጀመሪያ ሁለት ቀናት ከ130 በላይ ሃገራት መሪዎች በአየር ንብረት ለውጥ ፖሊሲዎች ላይ ይመክራሉ ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው በሁለተኛው ምዕራፍ የጉባኤው ቆይታም ሀገራት በአየር ንብረት ለውጥ ላይ በሰሯቸው ስራዎች ላይ በሚኒስትሮቻቸው በኩል ውይይት እንደሚደረግ የሚጠበቅ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም  በጉባኤው ላይ በፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ተፈፃሚነት ላይ ግምገማ የሚደረግ ሲሆን ኢትዮጵያም በአረንጓዴ አሻራ፣ በስንዴ ልማት እና በምግብ ስርዓት ላይ የሰራቻቸውን ስራዎች በአለም አቀፍ መድረኩ ላይ ተሞክሮዋን እንደምታካፍል ይጠበቃል ብለዋል የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ዴኤታ ክብር ዶክተር ነመራ ገበየው፡፡  
በአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የሚረዱ ግልጽ የሆኑ ማቀፎች እንዲዘረጉ፣ ቃል የተገቡ የፋይናንስ ድጋፎች ተገባራዊ እንዲሆኑ ጉባኤ ትልቅ ሚና ይጫወታል ሲሉ ተናግረዋል። 
ሀገሪቱ ከተባበሩት መንግስታት አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ የተሻለ ውጤት እንደምትጠብቅ አመላክተዋል። 

በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ጉባኤው በተለያዩ ጊዜያት በአየር ንብረት ለውጥ ለተጎዱ ታዳጊ ሃገራት ድጋፍ ለማድረግ የተገባ ቃልኪዳን ትግበራ ላይ ምክክር እንደሚደረግ እና የተለያዩ የሁለትዮሽ ውይይቶች እንደሚጠበቁ የተገለፀ ሲሆን ኢትዮጵያ በመድረኩ የምታንፀባርቀው አቋም ተለይቶ በልዑክ ቡድኑ በኩል የተለያዩ ዝግጅቶች ተካሂዷል ተብሏል፡፡

recent News
  • Image Here

    ኢትዮጵያ በ28ኛ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ለመሳትፍ ዝግጅቷን …

    04 April 2026
  • Image Here

    5ኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ውይይት (5th Africa Climate …

    04 April 2026
  • Image Here

    ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ምላሽ ለመስጠት ተግባራዊ …

    04 April 2026