Image Here

በኢፌዴሪ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር የተቋሙን አመራሮች እና ባለሙያዎች የበጀት አስተዳደር እና አዘገጃጀት የፋይናንስ አጠቃቀምና አስተዳደር አቅም ዕውቀትና ግንዛቤ ማሳደግ ያስቀመጣቸውን ስትራቴጂክ ግቦች ለማሳካት ወሳኝ ሚና እንዳለው አስታወቀ የካቲት 27/2017 ዓ.ም (ፕ.ል.ሚ.-አዳማ

የኢፌዴሪ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር የተቋሙን አመራሮች እና ባለሙያዎች የበጀት አስተዳደር እና አዘገጃጀት የፋይናንስ አጠቃቀምና አስተዳደር አቅም ዕውቀትና ግንዛቤ ያስቀመጣቸውን ስትራቴጂክ ግቦች ለማሳካት ወሳኝ ሚና እንዳለው አስታወቀ። ይህም የተገለጸው ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራሮች እና ለባለሙያዎች በ2018 ዓ.ም የበጀት ዝግጅትና የፋይናንስ አስተዳደርና አጠቃቀም ዙሪያ በአዳማ ከተማ ለሁለት ቀናት በተሰጠው የስልጠና መድረክ ላይ ነው።

በስልጠና መድረኩ ላይ በመገኘት የመክፈቻ መልዕክት ያስተላለፉት በሚኒስቴር መስርያ ቤቱ የብቃትና የሰው ሃብት አስተዳደር ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ እሸቱ አድማሱ ስልጠናው የተያዘለትን ግብ እንዲመታ ሁሉም የስልጠናው ታዳሚ አመራሮች እና ባለሙያዎች የሚጠበቅባቸውን ሚና በጥብቅ ዲሲፕሊን እንዲወጡ አመላክተዋል።

በተመሳሳይ መልኩ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ አቶ አስራት ተረዳ ስለ አጠቃላይ ስልጠናው ይዘት ሂደት ዓላማና ግብ በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን ሁሉም የተቋሙ የበጀት ዝግጅት የፋይናንስ አስተዳደር እና አጠቃቀም ባለድርሻ አካላት በጉዳዪ የሚታዩ የዕውቀት የግንዛቤ የማስፈፀም አቅም ክፍተቶችን ለመሙላት መታቀዱንና መደራጀቱን በመዘርዘር በትኩረት መከታተልና መለማመድ እንደሚያስፈልግ በአትኩሮት ገልፅዋል።

ስልጠናው በፕሮግራም በጀት አዘገጃጀት የስራዓተ ጾታ ጉዳዮች በበጀት አካቶ ትግበራና በፋይናንስ አጠቃቀም ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ሲሆን ከገንዘብ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በመጡ ባለሙያዎች በተግባራዊ ልምምድ የታገዘ ስልጠና ተሰጥቷል

recent News
  • Image Here

    በኢፌዴሪ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር የተቋሙን አመራሮች እና ባለሙያዎች …

    04 April 2026
  • Image Here

    በፕላንና ልማት ሚኒስቴር ከሰኔ 9 እስከ ሰኔ 11 …

    04 April 2026
  • Image Here

    ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በፕላንና …

    04 April 2026