አዲስ አበባ | ሰኔ 23/2017 ዓ.ም
ክብርት ዶ/ር ፍፁም አሰፋ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር እ.ኤ.አ. የ2025 የአለም የህዝብ ቁጥር ሪፖርት በሀገር አቀፍ ደረጃ ይፋ በሚደረግበት እና የአለም ህዝብ ቀንን አስመልክቶ በሚደረገው ዝግጅት ላይ ከኢትዮጵያ የUNFPA ተወካይ ሚስተር ኮፊ ኩዋሜ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።
በውይይታቸውም ሁለቱም ወገኖች ቁልፍ የህዝብ እና የልማት ጥያቄዎችን ለመፍታት ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል። ተጨማሪ የትብብር መስኮችን ላይ ስትራቴጂያዊ አጋርነታቸውን ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ተነጋግረዋል። ክብርት ዶ/ር ፍፁም እና ሚስተር ኩዋሜ በሚኒስቴሩ እና በUNFPA መካከል ያለው ትብብር ወደፊትም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተስማምተዋል።