Image Here

ኢትዮጵያ የምዘና ስርአትን በሀገርና በአፍሪካ እንዲስፋፋ ከአፍሪካና ከኢትዮጵያና የምዘና ማህበራት ጋር በጋራ ለመስራት የተጀመረውን ስራ አጠናክራ እንደምትቀጥል የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ፍጹም አሰፋ ገለፁ።

ኢትዮጵያ የምዘና ስርአትን በሀገርና በአፍሪካ እንዲስፋፋ ከአፍሪካና ከኢትዮጵያና የምዘና ማህበራት ጋር በጋራ ለመስራት የተጀመረውን ስራ አጠናክራ እንደምትቀጥል የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ፍጹም አሰፋ ገለፁ።

==========================================================================

አዲስ አበባ | ሰኔ 9/2017

ክብርት ሚኒስትሯ ይህንን የገለፁት ዛሬ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ተከብሮ በዋለው 25ኛ ዓመት የአፍሪካ የምዘና ማህበር የምስረታ በአል መክፈቻ ላይ ነው። ዶ/ር ፍጹም በእለቱ እንደተናገሩት የአፍሪካና የምዘና ማህበር ላለፉት ሩብ ምዕተ-አመታት በአህጉሪቱ ግምገማን በማስተዋወቅ ረገድ የልህቀት ምልክት ሆኖ ቆይቷል፡፡

25ኛው የምስረታ በአል በኢትዮጵያ መከበሩ በምሳሌነቱና ብቻ ሳይሆን በጣም ተገቢ እንደሆነ የገለፁት ዶ/ር ፍጹም አዲስ አበባ የአፍሪካ አንድነት ማዕከል መሆኗን ፣ የፖሊሲ የሃሳብ ንግግሮች እና የተቋማት እድገትን ማሳያ ጭምር ነው ብለዋል። በዚሁ መሰረት የፕላንና ልማት ሚኒስቴር የምዘና ስርአት እንዲሰፋፋ ከአፍሪካና ከኢትዮጵያና የምዘና ማህበራት ጋር በቅርበት ለመስራት የተጀመረውን ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል፡፡

ዶ/ር ፍጹም ፕላንና ልማት ሚኒስቴር በፌዴራል የመንግስት ተቋማት ላይ ተጨባጭ የምዘና ርምጃ እያካሄደ መሆኑን ጠቁመው የሀገር አቀፍ የግምገማ ፖሊሲ ማዕቀፍ በማዘጋጀትና በመተግበር፤ በአስር አመት መሪ የልማት እቅድ የምዘና ስርአትን በማካተት ፤ የህዝብ ኢንቨስትመንቶች ወቅታዊ እና ጥብቅ ምዘናዎች የሚደረግባቸው መሆኑና የ‹‹አንድ ዕቅድ አንድ ሪፖርት›› ሥርዓትን ማስተዋወቅ መቻሉና የክትትልና ግምገማ ስርዓታትን ዲጅታላይዜሽን ማድረግ በምዘና ሂደት በሀገሪቱ ከተከናወኑ ቁልፍ ስኬቶች ዋና ዋናዎቹ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

recent News
  • Image Here

    ኢትዮጵያ የምዘና ስርአትን በሀገርና በአፍሪካ እንዲስፋፋ ከአፍሪካና ከኢትዮጵያና …

    04 April 2026
  • Image Here

    04 April 2026
  • Image Here

    04 April 2026