የኢትዮጵያ የሥነ-ህዝብና ጤና ጥናት መረጃ የማሰባሰብ ሂደት በስኬት ተጠናቀቀ፡፡
**************************************************************************************
የኢትዮጵያ የሥነ-ህዝብና ጤና ጥናት አብይ ኮሚቴ እንደገለጸው በአገር አቀፍ ደረጃ የሥነ-ህዝብና ጤና ጥናት መረጃ የማሰባሰብ ሂደት 100% የተጠናቀቀ ሲሆን ይህም በተለያዩ ቁልፍ ዘርፎች ማስረጃ ላይ የተመሰረተ እቅድ እና ፖሊሲ ማውጣትን ለማሳደግ ወሳኝ እርምጃ እንደሆነ ተጠቁሟል።
የመረጃ አሰባሰቡ በመጠናቀቁ፣ ሂደቱ አሁን ወደ መረጃ ማቀናበር፣ ትንተና እና ሪፖርት አጻጻፍ የተሸጋገረ ሲሆን ይህም ስለ ኢትዮጵያ ጤና እና ስነ-ሕዝብ መገለጫ ወሳኝ ግንዛቤዎችን ለማግኘት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ተብሏል።