Image Here

የአረንጓዴ አሻራ ለአየር ንብረት ለውጥ ለመቋቋም ቁልፍ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የአረንጓዴ አሻራ ለአየር ንብረት ለውጥ ለመቋቋም ቁልፍ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ነሐሴ 7/2016 አዲስ አበባ (የፕ.ል.ሚ)

“አረንጓዴ አሻራ ለአየር ንብረት ለውጥ ያስገኘው ፋይዳ” በሚል ርዕስ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ከዓለም አቀፉ የአረንጓዴ እድገት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የከፍተኛ ደረጃ የፓናል ውይይት በራዲሰን ብሉ ሆቴል ተካሂዷል፡፡

የፓናል ውይይቱ ኢትዮጵያ እየወሰደቻቸው ካሉ ወሳኝ የአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ እርምጃዎች መካከል አንዱ በሆነው የአረንጓዴ አሻራ ላያ ትኩረቱን ያደረገ ሲሆን የሀገራችን ከፍተኛ አመራሮች፣ በሀገራችን የሚገኙ የተባበሩት መንግስታት እና የአፍሪካ ህብረት ኤጀንሲዎች/United Nation & African Union Agencies/፣ የጎረቤት ሀገራት አምባሳደሮች ፣የኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ አጋር ሀገራት ኢምባሲ አምባሳደሮች፣ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅቶች፣ የሲቪክ ማህበራት እና የግሉ ዘርፍ ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

የአረንጓዴ አሻራ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋምና ሁሉ አቀፍ አረንጓዴና ዘላቂ ኢኮኖሚ ለመገንባት የተወጠነ አገር በቀል መርሃ ግብር ነው ያሉት ፕላንና ልማት ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ፍጹም አሰፋ አረንጓዴ አሻራ ተፈጥሮን በማከም ይዞ የሚመጣው ትሩፋት ዘርፈ ብዙ ነውና ለትውልድ የሚተርፍ ቅርስን የሚያስቀር በመሆኑ የዘንድሮውን የ2016 የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብራችንን “የምትተክል ሀገር፣ የሚያጸና ትውልድ/ A Nation that Plants, A Generation that Sustains” ተብሎ ተሰይሟል። በዚህም መሰረት በዘንድሮው መርሃ ግብራችን 7.5 ቢሊዮን ችግኞች ለመትከል መላው የአገራችን ህዝብ በስራ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

ክብርት ሚኒስትሯ “ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ቀርጻ ላለፉት አምስት ዓመታት ባከናወነችው ያላሰለሰ ጥረት የአገራችንን የደን ሽፋን መጠን በሳይንሳዊ መንገድ ተጠንቶ እ.ኤ.አ በ2019 ከነበረበት 17.2 በመቶ በ2023 ወደ 23.6 በመቶ መድረሱን ስገልጽ በታላቅ ኩራትና ደስታ ነው” ብለዋል፡፡ በቀጣይ ጥቂት ዓመታት በምናደርገው ርብርብር እ.አ.አ. በ2030 የሀገራችን የደን ሽፋን 30 በመቶ ለማድረስ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

አክለውም ክብርት ሚኒስትር ዶ/ር ፍጹም አሰፋ አረንጓዴ አሻራ ለደን ሽፋን ከሚያደርገው አስተዋጽኦ ባሻገር የምግብ ዋስተናችንን እያረጋገጥን የምንገኝበት፣ የህብረተሰባችንን ኑሮ እያሻሻልን ያለንበት፣ የውሃ አቅርቦትን ለሀገራችንና ለጎረቤት ሀገራት በረከት የምንለግስበት፣ የኢነርጂ አቅርቦታችንን በታዳሽ ኃይል የምናስፋፋበት በአጠቃላይ በ10 ዓመቱ የልማት እቅዳችን ያስቀመጥነውን ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ልማት እያሳካን የምንገኝበት ቁልም መሳሪያችን ሆኖ ላለፉት አምስት ዓመታት በስኬት ተጉዘናል ብለዋል።

በኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ አረንጓዴ ዕድገት ኢንስቲትዩት ቢሮ ዳይሬክተር ኦኬቹኩ ዳንኤል ኦግቦናያ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በድፍረት እና ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት የአየር ንብረት እርምጃዎችን እያስተዋወቀች ነው። እስካሁን ከተወሰዱት ቁርጠኛ እርምጃዎች መካከል ከአረንጓዴው አሻራ ጋር የሚወዳደር አላገኘውም ብለዋል።

የዓለም አቀፉ አረንጓዴ ዕድገት ኢንስቲትዩት (GGGI) የኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራን በሀብት ማሰባሰብ፣ በፖሊሲ ምክር፣ በአቅም ግንባታ፣ በተቋማዊ ማጠናከሪያ ጥረቶች እና በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች በመሬት ላይ ያሉ ማህበረሰብ አቀፍ ፕሮጀክቶችን በመደገፍ በንቃት እና በተግባራዊ ሁኔታ ሲሰራ መቆየቱንና ወደፊትም እንደሚሰራ አንስተዋል።

ክብርት ሚኒስትሯ በመዝግጊያ ንግግራቸው የዛሬው መድረክ በእርግጥም ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማዕቀፍ ውስጥ እየተደረጉ ላሉ የእርምጃ ይወሰድ ጥሪ ከበቂ በላይ ምላሽ እየሰጠች እንደሆነ ያመላከተ ሲሆን ለሀገራችን ህዝቦች በ10 ዓመቱ የልማት እቅድ አማካይነት የገባነውን ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ እየገነባን እንደሆነ ማሳያ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡ ስለሆነም እዚህ ክፍል የምትገኙም ሆነ ሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቹን የፋይናንስ፥፣የቴክኖሎጂ አቅርቦትና የቴክኒክ ድጋፍ በማድረግ እንድትተባበሩን በራሴና በኢትዮጵያ መንግስት ስም እጠይቃቹኃለሁ ብለዋል።

recent News
  • Image Here

    የአረንጓዴ አሻራ ለአየር ንብረት ለውጥ ለመቋቋም ቁልፍ ሚና …

    04 April 2026
  • Image Here

    04 April 2026
  • Image Here

    04 April 2026