Image Here

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ክብርት ዶክተር ፍፁም አሰፋ ከአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ኃላፊ ጋር በልማት፣ በድጋፍ እና በአየር ንብረት ጉዳዮች ላይ ቁልፍ ውይይት አደረጉ።

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ክብርት ዶክተር ፍፁም አሰፋ ከአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ኃላፊ ጋር በልማት፣ በድጋፍ እና በአየር ንብረት ጉዳዮች ላይ ቁልፍ ውይይት አደረጉ።

ሐምሌ 18/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ (የፕ.ል.ሚ)

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ክብርት ዶክተር ፍፁም አሰፋ ከአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ኃላፊ ጋር በልማት፣ በድጋፍ እና በአየር ንብረት ጉዳዮች ላይ ቁልፍ ውይይት አደረጉ።

ክብርት ሚኒስትሯ በ4ኛው ዓለም አቀፍ ፋይናንስ ለልማት ጉባኤ (FfD) የዝግጅት ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ከተገኙት የአውሮፓ ህብረት የአለም አቀፍ አጋርነት (INTPA) የዘላቂ ፋይናንስ ዳይሬክተር አንቲ ካርሁነን ጋር ውጤታማ ውይይት አድርገዋል::

በቅርቡ በጎፋ ዞን በደረሰው የመሬት መደርመስ ባስከተለው አሰቃቂ የሰው ህይወት መጥፋት በአውሮፓ ህብረት ስም ማዘናቸውን ዳይሬክተሩ የተናገሩ ሲሆን የአውሮፓ ህብረት የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን እና አሁን ላይ ኮሚሽኑ ከኢትዮጵያ ፌደራል የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን እየሰራ በሚገኘው ቡድን በኩል እየተሰራ እንደሆነ ገልፀዋል። የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ክብርት ዶክተር ፍፁም በበኩላቸው ለአውሮፓ ህብረት ፈጣን ምላሽ አድናቆታቸውን ገልፀው አፋጣኝ ሰብአዊ ድጋፍ ጎን ለጎን ዘላቂ የአየር ንብረት መላመድ እስትራቴጂ እንደሚያስፈልግ አፅንዖት ሰጥተዋል።

በሁለትዮሽ ውይይቱ ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር የምታደርገውን ጥረትም ተመልክቷል። ክብርት ሚኒስትሯ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነትን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት በወሰዳቸው እርምጃዎች ላይ በጥልቀት አብራርተዋል። በመሆኑም የሽግግር የፍትህ ስርዓት የህግ ማዕቀፍ ዝግጅት ሊጠናቀቅ መቃረቡን የገለጹ ሲሆን ከዚሀ በተጨማሪ የብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን መቋቋሙ  በአገሪቱ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ወሳኝ ነው ብለዋል።

በተጨማሪም ክብርት ሚኒስትሯ የኢትዮጵያን የሀገር ውስጥ ኢኮኖሚ ማሻሻያ I ላይ ገለፃ በማድረግ የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ ተወዳዳሪነት እና የኢንቨስትመንት መስህብነት በማጎልበት የተመዘገቡ ስኬቶችን አውስተዋል። ኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ የሀገር ውስጥ ግጭቶች፣ የዩክሬን ጦርነት እና በምስራቅ እና ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ የተከሰቱ እንደ ድርቅ ያሉ የአየር ንብረት ነክ ጉዳዮች አንዳንድ የማሻሻያ ጥረቶች እንዲስተጓጎሉ እንዳረጉ አመላክተዋል፡፡ የሃገር ውስጥ የኢኮኖሚ ማሻሻያ II (Homegrown Economic Reform II) ሌላኛው የውይይቱ ትኩረቱ እንደነበረ ለመረዳት ተችሏል።

 

ሚስተር ካርሁነን የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና አረንጓዴ ሽግግር እንዲሁም በአለም አቀፍ ጌትዌይ እስትራቴጂ ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት ገልፀዋል። በአውሮፓ ህብረት ሁለገብ አመታዊ አመላካች ፕሮግራም (MIP) ስር ለኢትዮጵያ የተመደበውን 650 ሚሊዮን ዩሮ አንዱ የድጋፉ አካል መሆኑን አንስተዋል።

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ክብርት ዶክተር ፍፁም አሰፋ የኢትዮጵያን መንግስት በሁለገብ አመታዊ አመላካች ፕሮግራም (MIP) በማቀድና ትግበራ ላይ ማሳተፍ በአገሪቱ ቅድሚያ በሚሰጣቸው የልማት እንቅስቃሴዎች ጋር እንዲጣጣም በማድረግ ረገድ ያለውን ጠቀሜታ ያሰገነዘቡ ሲሆን ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ወሳኝ የሆነው የአውሮፓ ህብረት የበጀት ድጋፍ እንደገና እንዲጀመርም ጥሪ አቅርበዋል።

ሚኒስትሯ አያይዘውም በአዲሱ የአውሮፓ ህብረት የደን ጭፍጨፋ-ነጻ ደንብ (EUDR) ስጋት እንዳደረባቸው ገልጸዋል። የተጣደፈ ትግበራ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ቡና አምራቾችን ሊጎዳ እንደሚችል እና የአውሮፓ ህብረት የደን ጭፍጨፋ-ነጻ ደንብ (EUDR) ከአለም አቀፍ የአየር ንብረት ስምምነቶች ትክክለኛ የሽግግር መርሆዎች ጋር ሙሉ በሙሉ መጣጣም እንዳለበት  አንስተዋል። በመሆኑም ኢትዮጵያ  የEUDR መስፈርቶችን ለማሟላት ያላትን ቁርጠኝነት ገልፀው ለትግበራው የሚረዳ ተጨማሪ ግዜ እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል፡፡

recent News
  • Image Here

    የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ክብርት ዶክተር ፍፁም አሰፋ ከአውሮፓ …

    04 April 2026
  • Image Here

    04 April 2026
  • Image Here

    የኢትዮ- ሳውዲ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ፎረም በአዲስ አበባ …

    04 April 2026