Image Here

የኢትዮ- ሳውዲ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ፎረም በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም መካሄድ ጀመረ።

ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ(የፕ.ል.ሚ)
የኢትዮ- ሳውዲ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ፎረም በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም መካሄድ ጀመሯል።
በፎረሙ በሳውዲ ዓረቢያ የንግድ ምክር ቤት ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሁሴን ሙጂብ የተመራ 79 አባላት ያለው ልዑክ እና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በፎረሙ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ፍፁም አሰፋ፤ የሁለቱ ሀገራት የንግድ እና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንትን የሚያበረታታ 2ኛውን ምዕራፍ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም መተግበር መጀመሯንም አስታውቀዋል ክብርት ሚኒስትር፡፡
መንግሥት የንግድ ዘርፉን ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ማድረጉን ያስረዱት ክብርት ሚኒስትሯ፥ ከሕግ፣ አሠራርና መሰረተ-ልማት አኳያም የውጭ ኢንቨስተሮችን የሚያበረታታ ምቹ ምኅዳር መኖሩን ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ የካፒታል ማርኬት መጀመርን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ሪፎርም በማድረግ ለኢንቨስተሮች ምቹ ሁኔታ ፈጥራለች ነው ያሉት።
በመሆኑም የሳዑዲ ባለሀብቶች በማምረቻ ኢንደስትሪ፣ ቱሪዝም፣ ማዕድን፣ ታዳሽ ኃይል፥ ግብርናና በሌሎች የኢንቨስትመንት መስኮች እንዲሰማሩ ጥሪ አቅርበዋል።
ፎረሙም የሁለቱን ሀገራት የንግድ ትስስር ያጠናክራል ያሉት ዶ/ር ፍጹም አሰፋ፤ በርካታ የሳዑዲ አረቢያ ባለሀብቶች ኢትዮጵያ ውስጥ እየሰሩ ነው ያሉ ሲሆን ከዚህ የበለጠ ትብብር እንዲኖር የኢትዮጵያ መንግሥት ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል።
የሳውዲ ዓረቢያ የንግድ ምክር ቤት ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሁሴን ሙጂብ በበኩላቸው፤ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ከፈረንጆቹ 1948 የተጀመረ መሆኑን ገልፀው፤ አሁን ላይ ያለው የንግድ ግንኙነት ይህን የረጅም ጊዜ ግንኙነት የሚገልፅ ባለመሆኑ ግንኙነታችንን ልናጠናክር ይገባል ብለዋል።
ሳዑዲ ከአፍሪካ ጋር ያላትን የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት የማጠናከር ፍልጎት አላት ያሉት ፕሬዚዳንቱ በተለይም ከኢትዮጵያ ጋር በጋራና በትብብር የመስራት ፍላጎት አላት ብለዋል።  የልዑካኑ አባላት ከተለያዩ የንግድና አንቨስትመንት ዘርፎች የተወጣጡ መሆናቸዉን የተናገሩት ዶ/ር ሁሴን ሙጂብ ይህም ከኢትዮጵያዊያን ባለሃብቶች ጋር በጋራ ለመስራት ይረዳል ብለዋል።
በኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤትና በሳዑዲ አረቢያ ንግድ ምክር ቤት ፌዴሬሽን መካከል በጋራና በትብብር ለመስራት የሚያስቺል የመግባቢያ ስምምነት ተፈርሟል።
 ከፎረሙ አስቀድሞ የኢትዮጵያን የቆዳ፣ ጨርቃጨርቅ፣ ማዕድንና ሌሎች ምርቶችን እንዲሁም የቱሪዝም መዳረሻዎችን የሚያሳይ ዐውደ-ርዕይ ተጎብኝቷል። በሳዑዲ ዓረቢያ የንግድ ምክር ቤት ፌዴሬሽን የተመራ 79 አባላትን የያዘ ከፍተኛ የኢንቨስትመንትና የንግድ ልዑክ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ትናንት ማምሻውን አዲስ አበባ መግባቱ ይታወሳል።

recent News
  • Image Here

    የኢትዮ- ሳውዲ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ፎረም በአዲስ አበባ …

    04 April 2026
  • Image Here

    የአዉሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የሚያደርገዉን የልማት ትብብር እንደሚያጠናክር ገለጸ

    04 April 2026
  • Image Here

    04 April 2026