ኢትዮጵያ ከዩኒሴፍ ጋር በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ያላትን ትብብር እንደምታጠናክር አስታወቀች፡፡
******************************************************************************
ግንቦት 8/9/2016 አዲስ አበባ (የፕ.ል.ሚ)
ኢትዮጵያ ከዩኒሴፍ ጋር በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ያላትን ትብብር እንደምታጠናክር አስታወቀች፡፡
የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ስዩም መኮንን እና የዩኒሴፍ የኢትዮጵያ ምክትል ተወካይ ማሪኮ ካጎሺማ የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ስራዉ የህጻናትን ታሳቢና መሰረት ባደረገ መልኩ እንዲሆን ለማስቻል ትብብርን ማሳደግ ላይ ያተኮረ ሰፊ ስትራቴጂካዊ ውይይቶችን አድርገዋል።
ውይይቱ ግብአትን ለማሰባሰብ፣ ተቋማዊ አቅምን ለማጎልበት፣ የአየር ንብረት መረጃ አያያዝ ስርዓትን ለመዘርጋት፣ ህጻናትን ያማከለ የአየር ንብረት እንቅስቃሴ ግንዛቤን ለማሳደግ፣ የአየር ንብረት ፖሊሲዎችን በመቅረጽ እና በአለም አቀፍ ደረጃ በአየር ንብረት ጉዳዮች ላይ መሳተፍ ላይ ያተኮረ ነበር።
ሁለቱም ወገኖች ህጻናትን ከአየር ንብረት ለውጥ አሉታዊ ተፅእኖዎች የመጠበቅን አስፈላጊነት አጽንኦት ሰጥተዋል። ለመጪው SB60 እና COP29 የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።
ይህ ስብሰባ የኢትዮጵያ መንግስት እና ዩኒሴፍ ለህጻናት ደህንነት ቅድሚያ የሚሰጡ የአየር ንብረት እርምጃዎችን ለማስተዋወቅ ያደረጉትን ቁርጠኝነት ለማረጋገጥ ወሳኝ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።