Image Here

ኢትዪጵያና ጄርመን የጀመሯቸዉን የአየር ንብርት ለዉጥ የመከላከል የትብብር ስራዎች አጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ አረጋገጡ።

  

ኢትዪጵያና ጄርመን የጀመሯቸዉን የአየር ንብርት ለዉጥ የመከላከል የትብብር ስራዎች አጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ አረጋገጡ።

********************************************************************************************

አዲስ አበባ ፥ ግንቦት 1/2016 ዓ.ም (የፕ.ል.ሚ)

ኢትዪጵያና ጄርመን የጀመሯቸዉን የአየር ንብርት ለዉጥ የመከላከል የትብብር ስራዎች አጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ አረጋገጡ።

የጄርመን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የአለማቀፍ የአየር ንብርት ተግባራት ልዩ መልዕክተኛ ጄኔፈር ሊ ሞርጋን ከፕላንና ልማት ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አቶ ስዩም መኮንን ጋር ተወያይተዋል።

በዉይይቱ ክቡር ሚኒስትር ዲኤታዉ ኢትዮጵያ ለታዳሽ ሃይል ልማት እና የኢነርጂ ተደራሽነትን ለማሳደግ ያላትን ቁርጠኝነትን አብራርተዋል። የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብና የኮይሻ የኤልክትሪክ ማመንጫን በአብነትነት አንስተዉ ያብራሩት አቶ ስዩም መኮንን ኢትዮጵያ የጎረቤት ሃገራትን በታዳሽ ሃይል ኤክስፖርት እያስተሳሰረች መሆኑንም ገልጸዋል።

የጀርመን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የአለማቀፍ የአየር ንብርት ተግባራት ልዩ መልዕክተኛ ጄኔፈር ሊ ሞርጋን በበኩላቸዉ ጀርመን የኢትዮጵያን የታዳሽ ሃይል ልማት ለመደገፍ ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል።

በዉይይቱ ላይ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ እቅድ (NDC) እንዲሁም በአየር ንብረት ፋይናንስ ላይ ያሉ ተግዳሮቶች ምክክር የተደረገባቸዉ ሲሆን ኢትዮጵያ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ እቅድ (NDC) ላይ ክለሳ ለማድረግ እቅድ የያዘች መሆኑንም ሚኒስትር ዲኤታዉ አቶ ስዩም መኮንን አብራርተዋል ። በአየር ንብረት ፋይናንስ አቅርቦትና ተደራሽነት ላይ ያለው ክፍተትም ሰፊ ዉይይት ተደርጎበት በሀገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያንና በዝቅተኛ የእድገት ደረጃ የሚገኑ ሀገራት ተጠቃሚነት በሚያሳድጉ ጉዳዮች አብሮ ለመስራት ተስማምተዋል።

ጀርመን በኢትዮጵያ የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ እና አቅምን ለማሳደግ ፍላጎት እንዳልትም በዉይይቱ ተጠቁሟል። በተለይም የአየር ንብረት መረጃን የመሰብሰብ እና የመተንተን አቅምን ለማሳደግ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎት አላት። ጠንካራ የአየር ንብረት መረጃ ስርዓት መመስረት በሁለቱ ሃገራት ትብብር ቅድሚያ ተሰጥቷል፣ ይህም በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ አሰጣጥ እና ውጤታማ የፖሊሲ ትግበራን እዉን ለማድረግ አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበታል።

recent News
  • Image Here

    ኢትዪጵያና ጄርመን የጀመሯቸዉን የአየር ንብርት ለዉጥ የመከላከል የትብብር …

    04 April 2026
  • Image Here

    04 April 2026
  • Image Here

    04 April 2026