የፕላንና ልማት ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ፍጹም አሰፋ ከአለማቀፉ የገንዘብ ተቋም የኢትዮጵያ ተወካይ ቶቢያስ ናይቦ ጋር በጽህፈት ቤታቸዉ ተወያዩ፡፡
*****************************************************************************************************************
የካቲት 5 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ(የፕ.ል.ሚ)
የፕላንና ልማት ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ፍጹም አሰፋ ከአለማቀፉ የገንዘብ ተቋም የኢትዮጵያ ተወካይ ቶቢያስ ናይቦ ጋር በጽህፈት ቤታቸዉ ተወያዩ፡፡
በዉይይታቸዉም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በትብብር እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡
በቀጣይ ሶስት አመታት የሚተገበረዉን እና ሰሞኑን ይፋ የሆነዉን የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ ልማት ፕሮግራም ይዘቶች ያብራሩት ክብርት ሚኒስትር ዶ/ር ፍጹም አሰፋ አይ ኤም ኤፍ በዚህ ረገድ ያለዉን ልምድና የቴክኒክ አቅም ለኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች እንዲዲያካፍል ጠይቀዋል፡፡ በኢኮኖሚ ስታትስቲክስ እንዲሁም በፐብሊክ ኢንቨስትመንት አስተዳደር ላይም የቴክነክ ድጋፍ በማድረግ በትብብር ለመስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል፡፡
የአለማቀፉ የገንዘብ ተቋም የኢትዮጵያ ተወካይ ቶቢያስ ናይቦ በበኩላቸዉ ተቋሙ ያለዉን ልምድና ተሞክሮ በማካፈል የትብብር ስራዉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡