Image Here

ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ምላሽ ለመስጠት ተግባራዊ ባደረገቻቸው ፖሊሲና ስትራቴጂዎች ተጨባጭ ለውጥ ማምጣቷል የፕላንና ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ።

አዲስ አበባ ሐምሌ 7/2015 (የፕ.ል.ሚ)

 

 ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ምላሽ ለመስጠት ተግባራዊ ባደረገቻቸው ፖሊሲና ስትራቴጂዎች ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት እንደቻለች የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ገለጸ።

ሚኒስቴሩና የተጠሪ ተቋማት  2015 . የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያና መርሃ-ግብሩ የአረንጓዴ አሻራ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን በመቋቋም ለምጣኔ ሀብት እድገትና ልማት በሚኖረው አስተዋጽኦ ላይ የፓናል ውይይት አካሂዷል።

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ጥሩማር አባተ እንደገለጹት መንግስት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ምላሽ ለመስጠት ፖሊሲ፣ ስትራቴጂ፣ የረዥም ጊዜ እቅድ በመቅረጽና ተቋማትን በማደራጀት ባከናወነው ተግባር ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ተችሏል።

በአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር ባለፉት አምስት አመታት ህብረተሰቡን በማሳተፍ 25 ቢሊዮን ችግኝ መትከል የተቻለ ሲሆን መርሀ ግብሩን ወደ ጎረቤት አገሮች ለማስፋት እየተሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

በተመሳሳይ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ ያላትን ልምድ በተለያዩ አለም አቀፍ መድረኮች እያስተዋወቀች ሲሆን በቀጣይም ልምዷን ለማካፈል ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር እየተሰራ መሆኑን አክለዋል።

ኢትዮጵያ .. 2050 የሙቀት አማቂ ጋዞች ልቀትን ዜሮ የማድረስ ራዕይ የያዘውን የረዥም ጊዜ ስትራቴጂ በቅርቡ ይፋ ማድረጓን አስታውሰዋል።

በመካከለኛ ጊዜ አረንጓዴ ምጣኔ ሀብትን መገንባትና የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም የአስር አመቱ የልማት እቅድ ዋነኛ ትኩረት በማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል።

በመሆኑም የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን በመከላከል ትልቅ ፋይዳ ባለው በአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብርና ሌሎች ፖሊሲና ስትራቴጂዎች ተጨባጭ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ተናግረዋል።

የተተከሉ ችግኞች ለውጥ እንዲያመጡም ክትትሎችን እንደሚያደርጉ ሚኒስትር ዴኤታዋ ገልጸዋል፡፡ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከልና ኢትዮጵያ ንፁህ አየር እንዲኖራት በማድረግ በዓለም ተመራጭ ሀገር ለማድረግ ሁሉም ትብብር ሊያደርግ እንደሚገባም አስረድተዋል፡፡

 

የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳሬክተር ዶክተር ጌታሁን ጋረደው፤ ኢትዮጵያ የአካባቢ ጉዳዮች ዘላቂነት የሚያረጋግጡ ፖሊሲና ስትራቴጂዎችን ተግባራዊ እያደረገች ትገኛለች ብለዋል።

የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር ባለፉት ዓመታት ያለአግባብ የተፈጥሮ ሃብትን ጥቅም ላይ በማዋል በአካባቢ ላይ የደረሰውን ጉዳት እየታደገ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

መርሀ ግብሩ የአገሪቱን የደን ሽፋንና የከርሰ ምድር ውሃ ሀብት ክምችትን በመጨመር፣ ሙቀት አማቂ ጋዝን በማመቅ ጤናማ አካባቢን በመፍጠር ያለውን ፋይዳ ዘርዝረዋል።

በተጨማሪም በህብረተሰብ ግንዛቤ ላይ ለውጥ በማምጣት የደን ጭፍጨፍ ላይ ከፍተኛ ለውጥ መታየቱን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

በተካሄደዉ የፓናል ዉይይት በዘርፉ ከፍተና ልምድና እዉቀት ያላቸዉ ዶ/ር ቢቂላ ወርቅነህ እና ዶ/ር ዘዉዱ እሸቱ የአረንጓዴ አሻራ ፋእዳዎች እንዲሁም ኢትዮጵያ በአለም መድረክ ያላትን ተሳትፎና ዉጤቶች በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ፥ ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የመጡት አቶ ተስፋዬ ደረሰም የመሬት አጠቃቀምና በደን ሽፋን ማደግን አስመልክተዉ የጥናት ጽሁፍ አቅርበዋል።

2015 . የፕላንና ልማት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በአጠቃላይ 41ሺህ ችግኞችን ለመትከልና ባለፉት ዓመታት የተተከሉትን የመንከባከብ ዕቅድም ተይዟል። መርሃ ግብሩን የግሎባል ግሪን ግሮዝ ኢንስቲትዩት (Global Green Growth Institute)ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር ጋር በመተባበበር የተዘጋጄ ሲሆን በአረንጓዴ ልማት ፥ በአካባቢ ጥበቃ ፥ አየር ንብረት ለዉጥ መከላከል ፥ በአረንጓዴ አሻራ እና ተዛማጅ ዘርፎች ላይ ያሉ የፈጠራ ስራዎችን ለማበረታታት የአረንጓዴ ሽልማት(Green Award)ተዘጋጅቷል።

 

 

recent News
  • Image Here

    ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ምላሽ ለመስጠት ተግባራዊ …

    04 April 2026
  • Image Here

    04 April 2026
  • Image Here

    04 April 2026