ኢትዮጵያ የ2023 የአለም የህዝብ ቀንን አከበረች።
************************************
ነሃሴ 30,2015 ዓ.ም ፥ አዲስ አበባ ፥ (የፕ.ል.ሚ)
ኢትዮጵያ የአለም ህዝብ ቀንን 2023"በኢትዮጵያ ውስጥ የማያልቁ እድሎችን መፍጠር የስርዓተ-ፆታ እኩልነትን ማረጋገጥ" በሚል መሪ ቃል አክብሯል።
በዝግጅቱ በአዲስ አበባ ሀያት ሬጀንሲ የተካሄደ ሲሆን የመንግስት ባለስልጣናት፣የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኤጀንሲዎች እና የሲቪክ ማህበራት ተወካዮች ተገኝተዋል።
የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ጥሩማር አባተ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ኢትዮጵያ የአዲስ አበባን የህዝብና ልማት ቃልኪዳን እና የ2030 የዘላቂ ልማት አጀንዳን ተግባራዊ ለማድረግ ያላትን ቁርጠኝነት አመልክተዋል። ዘላቂ ልማትን ለማስፈን የሥርዓተ-ፆታ UNFPA እኩልነት እና የሴቶችን አቅም ማጎልበት አስፈላጊነትንም አንስተዋል።

የአለም ህዝብ ቀን አከባበር ሴቶችን እና ልጃገረዶችን የማብቃት እና ከወንዶች እኩል መብትና እድሎች እንዲኖራቸው የማድረግን አስፈላጊነት ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር። ለሴቶች እና ልጃገረዶች የበለጠ ዘላቂ እና ፍትሃዊ የሆነ የወደፊት ዕጣ ፈንታ እንዲፈጠር ለማድረግ የተግባር ጥሪ ነበር ያስፈልጋል ብለዋል ክብርት ሚኒስትር ዲኤታ ወ/ሮጥሩማር አባተ።
የአስር አመቱ የልማት እቅድ በስርዓተ-ፆታ እኩልነት እና በማህበራዊ ማካተት ላይ በቂ ትኩረት ሰጥቷል ያሉት ወ/ሮ ጥሩማር አባተ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር በስነ-ሕዝብ ልማትና በተለይም በሥርዓተ-ፆታ እኩልነት ጉዳዮች ላይ የማያቋርጥ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
የተባበሩት መንግስታት የስነ-ህዝብ ፈንድ (UNFPA) የኢትዮጵያ ተወካይ ሚስተር ኮፊ ኮዋሜይ በዝግጅቱ ላይ ንግግር አድርገዋል። የሴቶችና ልጃገረዶች በህብረተሰብ ውስጥ ያላቸውን ሚና ለማጠናከር UNFPA ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን ገልጿል። የዓለማችንን ማለቂያ የሌላቸውን እድሎች ለመክፈት የሴቶችን እና ልጃገረዶችን ድምጽ ከፍ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል ።

በዝግጅቱ ላይ በኢትዮጵያ የዴንማርክ አምባሳደር በአዲስ አበባ የሚገኘውን የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ በመወከልም ንግግር አድረገዋል። አምባሳደሯ እንዳሉት ዴንማርክ ኢትዮጵያ የስርዓተ ጾታ እኩልነትን ለማስፈንና የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል።