Image Here

የፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የጀመራቸዉን ሁሉን አቀፍ የልማት ትብብሮች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ።

የፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የጀመራቸዉን ሁሉን አቀፍ የልማት ትብብሮች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ።
************************************************************************************************************
ታህሳስ 17/2016 አዲስ አበባ (የፕ.ል.ሚ) 
የፈረንሳይ የልማት ኤጄንሲ( ኤፍዲ) ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የጀመራቸዉን ሁሉን አቀፍ የልማት ትብብሮች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ።
የፕላንና ልማት ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ፍጹም አሰፋ የፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሉዊስ አንቶኒ ሶቼትን በጽህፈት ቤታቸዉ ተቀብለዉ አነጋግረዋል።
የኢትዮጵያና የፈረንሳይ ረዥም ጊዜን ያስቆጠረ የትብብር ግንኙነት አላቸዉ ያሉት ክብርት ሚኒስትር ዶ/ር ፍጹም አሰፋ ይህም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣ መሆኑን አመላክተዋል። 
በአገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም  ትግበራ ላይ የፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ ከፍተኛ ድጋፍ ማድረጉን ያነሱት ክብርት ሚኒስትሯ ከአስር አመቱ እቅድ ላይ ከተቀዳዉ የሶስት አመቱ የመካከለኛ ዘመን  እቅድ ትግበራ እና በሁለተኛዉ ምዕራፍ የሃገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም የትግበራ አመታትም ላይ  ይሄዉ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
 የፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሉዊስ አንቶኒ ሶቼት በበኩላቸዉ የፈረንሳይ መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር የሚሰራቸዉን የትብብር ስራዎች አጠናክሮ እንደሚሰራ ያረገገጡ ሲሆን ።  በሁለተኛው በአገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ትግበራ ላይ ድጋፉን እንደሚያጠናክር ተናግረዋል። በኢነርጂ በተለይም በታዳሽ ሃይል ልማት የትብብር ስራዎች መኖራቸዉን ያነሱት የኢትዮጵያ ዳይሬክተሩ በከተሞች ፕላን ፥ በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎች ልማት ፥ በግብርና ምርትና ምርታማነት ማሳደግና ኤክስፖርት ላይ በርካታ የትብብር ስራዎችን እየተሰሩ መሆኑን አንስተዋል።

recent News
  • Image Here

    የፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የጀመራቸዉን ሁሉን …

    04 April 2026
  • Image Here

    04 April 2026
  • Image Here

    Ministry of planning and development in collaboration with …

    04 April 2026