Image Here

አየር ንብረት ለውጥ ምክንያት እየደረሱ ያሉ ችግሮችን ለመቋቋም የሚያስችል በጀት ያስፈልገናል:- የአፍሪካ የአካባቢ ሚኒስትሮች ጉባዔ

አየር ንብረት ለውጥ ምክንያት እየደረሱ ያሉ ችግሮችን ለመቋቋም የሚያስችል በጀት ያስፈልገናል:- የአፍሪካ የአካባቢ ሚኒስትሮች ጉባዔ
*****************************************************************************************************************
የአፍሪካ የአካባቢ ሚኒስትሮች ጉባኤ (AMCEN) አፍሪካ በኮፕ 28 የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ከፍተኛ አመራሮች ውይይት ላይ እንደ አህጉር ይዛ የምትቀርባቸው ዐቢይ ጉዳዮች ዙርያ እየመከረ ነው።
አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰባት ነው ያሉት የአፍሪካ የአካባቢ ሚኒስትሮች ጉባዔ ፕሬዚደንት እና የፕላንና ልማት ሚኒስትር ክብርት ዶክተር ፍፁም አሰፋ፤ ለዚህ ችግር የጋራ መፍትሄ ለማምጣትእንደ አህጉር  በጋራ መቆም ይገባናል ብለዋል።
በአፍሪካ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ያሉ ችግሮችን ለመከላከል፤ ተፈጥሮን ማዕከል ያደረገ አሰራር ሊተገበር ይገባል  ነው ያሉት የጉባዔው ፕሬዚደንት። 
ለዚህ ደግሞ የበለፀጉ ሀገራት እና የሚመለከታቸው አካላት የአየር ንብረትን ተከትሎ የሚመጡ ችግሮችን ለመከላከል ለሚሰራው ስራ ድጋፍ ማድረግ ይኖርባቸዋል ብለዋል።
የአፍሪካ የቴክኒክ ኮሚቴ እና ተደራዳሪ ቡድን፤ አፍሪካ በኮፕ 28ቱ የከፍተኛ አመራሮች ውይይት ልታንፀባርቃቸው እና አቋም ልትይዝባቸው ይገባል ብሎ በለያቸው ጉዳዮች ላይ ውይይቱ ያተኩራል።
በዚህም የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የሚያስችል ፋይናንስ ከበለፀጉ ሀገራት ለከፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ተጎጂ ሀገራት የሚለው አጀንዳ ቀዳሚው ሆኗል።
በውይይቱ የአፍሪካ አካባቢ ጥበቃ ሚኒስትሮች፣ ከአፍሪካ ኀብረት፣ ከአፍሪካ ልማት ባንክ እና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተወከሉ አመራሮች እየተሳተፉበት ነው።
@ኢቴቪ

recent News
  • Image Here

    አየር ንብረት ለውጥ ምክንያት እየደረሱ ያሉ ችግሮችን ለመቋቋም …

    04 April 2026
  • Image Here

    በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተለይም …

    04 April 2026
  • Image Here

    04 April 2026