Image Here

በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የሚገኙ ታላላቅ ኩባንያዎች የተሳተፉበት የቢዝነስ ፎረም ተካሄደ፣

በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የሚገኙ ታላላቅ ኩባንያዎች የተሳተፉበት የቢዝነስ ፎረም ተካሄደ፣ 
========================
እ.ኤ.አ ከኖቬምበር 30 እስከ ዴሴምበር 12 ቀን 2023 በዱባይ እየተካሄደ ባለው 28ተኛው የዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP28) ጎን ለጎን አገራችን ያላትን እምቅ የኢንቨስትመንት አቅም ለማስተዋወቅ ያገዘ የቢዝነስ ፎረም ተካሄዷል፡፡  በዚህ ፎረም ላይ በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የሚገኙና በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ አቅም ያላቸውን ከ30 በላይ ታላላቅ ኩባንያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ 

May be an image of 6 people and dais
በፎረሙ ላይ ክብርት የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ፍጹም አሰፋ አገራችን በአየር ንብረት ለውጥ ላይ እያስመዘገበች ስላለው ስኬት፣ በዘርፉ የግል ባለሀብቶች ሚናና በኢትዮጵያ ስላሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በተጨማሪም ክቡር የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴዔታ ዶ/ር ነመራ ገበየሁ፣ ክብርት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ምክትል ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ መልዕክተ ሳህሉ እና ክቡር አምባሳደር አክሊሉ ከበደ በተዘጋጁ ሁለት የፓናል ውይይቶች ላይ  በጉዳዩ ላይ ለተሳታፊዎች ገለጻ አድርገዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዕድሎች በመጠቀም ውጤታማ የሆኑ የቢዝነስ ድርጅቶች ጋር ሁለተኛ ክፍል የፓናል ውይይት ተካሂዷል። በውይይቱም በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጭ ዕድሎችን በመጠቀም ገብቶ መሥራት የሚያስገኟቸውን ጠቀሜታዎች ፓናሊስቶቹ ለታዳሚው አስረድተዋል።
በውይይቱ ማብቂያ ላይ በእንግድነት የተገኙት የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር  ልዩ አማካሪ ክቡር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ የፕሮግራሙ ማብቂያ ላይ የማጠቃለያ ሃሳብ በመስጠት ፕሮግራሙን ዘግተዋል።

recent News
  • Image Here

    በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የሚገኙ ታላላቅ ኩባንያዎች የተሳተፉበት የቢዝነስ …

    04 April 2026
  • Image Here

    04 April 2026
  • Image Here

    04 April 2026