Image Here

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ለመቄዶንያ በጎ አድራጎት ድርጅት የተለያዩ ድጋፎችን አደረገ፡፡

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ለመቄዶንያ በጎ አድራጎት ድርጅት የተለያዩ ድጋፎችን አደረገ፡፡
 *************************************************************************
ህዳር 5/3/2016 አዲስ አበባ (የፕ.ል.ሚ)
የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ለመቄዶንያ በጎ አድራጎት ድርጅት  የቢሮ መገልገያ ቁሳቁስ እና የንፅህና መጠበቂያዎች አበረከቷል፡፡
የሚኒስቴሩ ሰራተኞችና አመራር አካላት  የበጎነት ቀንን በጳጉሜ 3/2015 የመቄዶንያን መስራች የክቡር ዶክተር ቢኒያም በለጠ በመጋበዝ ማክበራቸው ይታወሳል፡፡በዚሁም ቀን በቅርቡ መቄዶንያን እንደሚጎበኝ እና ድጋፍ እንደሚደረግ በገቡት ቃል መሰረት ነው ድጋፉና ጉብኝቱ  የተደረገው፡፡
በተደረገው ድጋፍም የተለያዩ የመኪና መለዋወጫዎች፣ laptop ኮምፒውተር፤ ዴስክቶፕ፣ ፐሪንተር፣ መደርደሪያዎች፣ ቆርቆሮዎቸ እንዲሁም ለንፅህና መጠበቂያ ይውሉ ዘንድ የልብስና የእጅ ሳሙናና የአዋቂ ዳይፐሮች ይገኙበታል፡፡
በመቄዶንያ 7500 በላይ የአእምሮ ህሙማንና አረጋውያንን በመንከባከብ ላይ የሚገኝ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን 1200 ታካሚዎችን የሚያስተኛ አልጋ ያለው ሆስፒታልና የአረጋዊኣን መኖሪያን ያካተተ ህንጻ እየተገነባም ይገኛል። 

ከተቋሙ ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ በህንፃ ውስጥ የሴቶች፣ አረጋዊያን እና የአእምሮ ህሙማን ማረፊያዎች ፣የተለያዩ የእምነት ቦታዎች ፤ ግዙፍ ሆስፒታል፤ የእጅ ጥበብ እና የአርት ቴራፒ እንዲሁም የተቋሙ ጥቆማ መስጫ (8131) call center) እና የ8161 ሰርቨር በቆጣጠሪያ ጣቢያ  እንደሚኖሩት በጉብኝቱ መረዳት ተችሏል፡፡


በመቄዶንያ  በተለያዩ የአእምሮ ህመሞችና በአደጋ ምክንያት ጎዳና ወድቀው የነበሩና በተቋሙ ድጋፍ ከተደረገላቸው በኋላ ከህመማቸው ድነው ወደ ስራ በመመለስ ተቋሙን በሙያቸው እያገለገሉ እንደሚገኙ በጉብኝቱ ማየት ተችሏል፡፡
የበጎ አድራጎት ተቋሙ በአዲስ አበባ ከሚገኘው ስፍራ በተጨማሪ በክልል ቅርንጫፎች የመድሃኒት ፣የምግብ ፣የቁሳቁስና  አቅርቦት ከዚሁ ስለሚላክ በተለይም የመድሃኒት አቅርቦት ከፍተኛ ዕጥረት እንደሚገጥማቸው ማየት ተችሏል፡፡
የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ጥሩማር አባተ በርክክቡ ወቅት እንደተናገሩት የተደረገዉ ድጋፍ በቂ ባይሆንም ሌሎች ተቋማትን ለማነሳሳት እና ለማሳሰብ ያለመ እንደሆነ ጠቅሰው በተለይም ከነበሩበት ጎዳና ተነስተው ተለውጠው ማየት እጅግ ድስ የሚያስኝ ነገር እንደሆነ አስረድተዋል። ሁሉም ለመቄዶንያ  ያለዉን  ግዜ ጨምሮ ድጋፍ ቢያደርግ ከፍተኛ እርካታን የሚፈጥርና ለወገን መድረስ እንደሆነም ክብርት ሚኒስትር ዲኤታዋ ወ/ሮ ጥሩማር አባተ ተናግረዋል።


በተቋሙ የሚገኙት በአንድ ወቅት በትምህርት እና በኑሮ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የነበሩ ነገር ግን በህመምና በተለያዩ ችግሮች አልጋ ቁራኛ የሆኑ በመሆናቸው ከጎናቸው መቆምና ድጋፍ ማድረጋችንን  እንቀጥላለን ነው ያሉት ክብርት ሚኒስቴር ዴኤታዋ ፡፡
ወ/ሮ ጥሩማር አክለውም መቄዶንያ ትንሿን ኢትዮጵያ የምንናይበት የበጎ አድራጎት ተቋም በመሆኑ በቤታችን በቤሮአችን የማንጠቀምባቸው ቁሳቁሶችን እና አልባሳትን ከምንም በላይ ደግሞ ሰው ነውና ሚያስፈልጋቸው መተን በመጎብኘት ማህበራዊ ሃላፊነታችን እንወጣ የሚል መልዕክትም አስተላልፈዋል፡፡
የመቄዶንያ መስራች የክቡር ዶክተር ቢኒያም በለጠ በበኩላቸው ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከዚህም በፊት በርካታ ድጋፍ እንደተደረገላቸዉ አንስተዉ በዛሬውም ዕለት ለሚያስፈልጉን እና በዚህም ሰዓት አልቆብን የነበረ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ በማምጣት ለችግራችን የደረሰ ተቋም በመሆኑ ከፍተኛ ምስጋና አቀርባለሁ ብለዋል። 
                              

recent News
  • Image Here

    የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ለመቄዶንያ በጎ አድራጎት ድርጅት የተለያዩ …

    04 April 2026
  • Image Here

    የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ክብርት ዶክተር ፍፁም አሰፋ …

    04 April 2026
  • Image Here

    በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የሚገኙ ታላላቅ ኩባንያዎች የተሳተፉበት የቢዝነስ …

    04 April 2026