የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ለመቋቋም ያለመ አህጉር አቀፍ የምክክር መድረክ ተሳታፊዎች የወዳጅነት አደባባይን ጎበኙ፡
**************** ******** ******** ******** ******** ******** ******** ******** ******** ******** ********
መስከረም 23/1/2016 አዲስ አበባ (የፕ.ል.ሚ)
የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ለመቋቋም ያለመ አህጉር አቀፍ የምክክር መድረክ ተሳታፊዎች የወዳጅነት አደባባይን ጎበኙ፡፡
በፕላንና ልማት ሚኒስቴር አስተባባሪነት የተዘጋጀው የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ለመቋቋም ያለመ አህጉር አቀፍ የምክክር መድረክ 18 ሃገራትና የተለያዩ አለማቀፍ ተቋማት የተሳተፉበት ነዉ።
በጉብኝቱ ላይ ገለፃ ያደረጉት በፕላንና ልማት ሚኒስቴር የዓለም የአካባቢ ፋሲሊቲ (GEF) ተወካይ አቶ መንሱር ደሴ ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥና በአከባቢ ጥበቃ ላይ በርካታ ስራዎችን እየሰራች ትገኛለች ያሉ ሲሆን ለዚህም የወዳጅነት አደባባይ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡ በመሆኑም የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ለመቋቋም በተዘጋጀውን አህጉር አቀፍ የምክክር መድረክ ላይ ለተሳታፊ ሀገራት ተወካዮች ማስጎብኘት ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ተመሳሳይ ፐሮጀክቶችን እንዲተገብሩ መነሻ ሊሆን እደሚችል ገልፀዋል፡፡ አቶ መንሱር አያይዘውም የሀገራት መሪዎች በአየር ንብረት ለውጥና የአከባቢ ጥበቃ ላይ ትኩረት አድርገው ቢሰሩ የአየር ንብረት ለውጥን የምትቋቋም አፍሪካን ብሎም አለምን መፍጠር እንደሚቻል ጠቁመዋል፡፡
የጉብኝቱ ተጋባዥ እንግዳ የሆኑት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ (head center for envormental science)የአካባቢ ሳይንስ ማዕከል ዲን ዶክተር አህመድ ሀሰን በበኩላቸው ኢትዮጵያ ይሄንን የመሰሉ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን መቋቋም የሚያስችሉ ፕሮጀክቶችን ስትሰራ የአየር ንብረት ለውጥ ችግሮችን ከመቋቋም በተጨማሪ ለከተማ ኗሪዎች ምቹ የመኖሪያ ስፍራ ለመፍጠር፤የተለያዩ ሁነቶችን ለማከናወን እና ውብና ለእይታ ማራኪ የሆነ ከተማ ለመፍጠር እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በአለም አቀፍ የአከባቢ ፋሲሊቲ የአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ እስፔሻሊስት የሆኑት አሎክ ባርኗል የወዳጅነት አደባባይ ከኢትዮጲያን አልፎ ለሌሎች ሀገራት ዜጎች መዝናኛ ከመሆኑም በላይ ለሀገሪቷ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅእኖ እየተከላከለ የሚገኝ እና አዲስ አበባ እንደ ስሟ አዲስ ደማቅ ያደረገ ፕሮጅክት ነው ብለዋል፡፡
የወዳጅነት አደባባይ ፕሮጀክት በሌሎች ሀገሮች ሊከወን የሚችል የብህሃ-ህይወት ምንጭም ነው ብለዋል፡፡ከዚህም በተጨማሪም የወዳጅነት አደባባይ የተሰራበት መንገድ የኢትዮጲያን ብሔር ብሔረሰቦች ስያሜ እንዲሁም እያንዳንዱ የአደባባዩ አሰራር የራሱ ትርጉም ያለው መሆኑ ለየት ያደርገዋል ብለዋል፡፡
በዕለቱ ከወዳጅነት አደባባይ በተጨማሪ የኢትዮጲያ የአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ በደጋ የሀገሪቱ አከባቢ የዕቅዶች እና ፕሮጀክቶች አተገባበር፤ ያሉበት ሁኔታ፤ ያጋጠማቸው ችግሮችና የፈቱባቸውን መንገዶች እንዲሁም በማህበረሰቡ ያመጣውን ለውጥ ላይ የጋራ ውይይት ተደርጓል፡፡