Image Here

የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ለመቋቋም ያለመ አህጉር አቀፍ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ለመቋቋም ያለመ አህጉር አቀፍ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
************************
መስከረም 21/1/2016 አዲስ አበባ (የፕ.ል.ሚ) 
የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ለመቋቋም ያለመ አህጉር አቀፍ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ከአለም አቀፍ የአከባቢ ፋሲሊቲ (GEF) እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለዉጥ ማዕቀፍ ስምምነት (UNFCCC) ጋር በመተባበር በአየር ንብረት ለውጥ መላመድ ክልላዊ ፕሮግራም እና ስትራቴጂ በማደግ ላይ ባሉ ሀገሮች ላይ ትኩረቱን ያደረገ አውደ ጥናት አዘጋጅቷል።
መክፈቻ ላይ የተገኙት የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ክብር አቶ ሳንዶካን ደበበ በመክፈቻ ንግግራቸው አፍሪካ በለተይም ከአከባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት እንደ ጎርፍ፤ድርቅና ረሀብ የመሳሰሉ እግሮች እየተጋፈጠች መሆኑን አንስተው ለእንደዚህ አይነት ችግሮች መፍትሔ እንደ አለም አቀፍ የአከባቢ ፋሲሊቲ (GEF) ባለው ውስን ምንጭ በመጠቀም መስራት ተገቢ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡


ይህን ችግር ደግሞ መቀልበስ የሚያስችል አቅም አፍሪካ የሌላት መኾኑ ችግሩን አሳሳቢ ያደርገዋል ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው። አሁን ላይ ችግሩን ለመቅረፍ ታዳጊ ሀገራት ፓሊሲ ቀርፀው እና ማስፈጸሚያ ስልት ነድፈው እየሠሩ ቢኾንም ያደጉት ሀገራት ለዚህ ተግባር የሚያደርጉት የፋይናንስ ድጋፍ ግን በቂ አደለም ብለዋል። ይሁን እንጂ በዚህ ሁሉ ኹኔታ ውስጥ ኾኖም እንደ ግሎባል ኢንቫይሮመንት ፈሲሊቲ አይነት ተቋማት የሚያደርጉት ድጋፍ የሚመሠገን ነው ብለዋል።
ሚኒስቴር ዴኤታው አያይዘውም ኢትዮጲያ በአከባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳዮች ላይ በስፋት እየተንቀሳቀሰች ነው ያሉ ሲሆን የ10 ዓመት የልማት ዕቅዱም ላይ ትልቅ ቦታ በመሰጠቱ ምክንያት በአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር በአራት ዓመት ብቻ 25 ቢሊየን ችግኝ ለመትክል ታቅዶ 26 ቢሊየን በላይ ችግኝ መትከል መቻሉ ለሌሎች ሀገራት ሊተላለፍ የሚችል ጥሩ ልምድ ነው ብለዋል፡፡
በፕላንና ልማት ሚኒስቴር የዓለም የአካባቢ ፋሲሊቲ ተወካይ እንዲሁም የዓለም አቀፍ አካባቢ ስምምነቶች ድርጅት ማስተባበሪያ ዳይሬክተር አቶ መንሱር ደሴ ፣በዓለም አቀፍ ያሉ የአየር ንብረት ለዉጥ፣የብዝሀ ህይወት እንዲሁም የአካባቢ ብክለትን በተመለከተ ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ ሀገራት መፈራረማቸዉን ገልፀዋል። 
ከስምምነቱ በኋላ በትግበራ ላይ የሚገኘዉ ይህ ስምምነት፣ የአደጉ ሀገራት በማደግ ላይ ለሚገኙ ሀገራት ገንዘብ፣ ቴክኖሎጂ እና የአቅም ግንባታ ድጋፍ እንዲያደርጉ ስምምነት ላይ ተደርሷል ብለዋል። 
ገንዘቡ በተለያዩ መንገዶች ከአደጉ ሀገራት ወደ ታዳጊ ሀገራት እንደሚላክ የገለፁት አቶ መንሱር፣ ለኢትዮጵያ የተደረገዉ የአሁኑ ድጋፍ ወደ አለም አቀፉ የገንዘብ ቋት በሆነዉ የአለም አካባቢ ፋሲሊቲ አማካኝነት መሆኑን ገልፀዋል። 
በመድረኩ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ድጋፍ (LDCF) በአከባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳዮች ፣ በውሀ እና ኢነርጂ ፣ በግብርና፣ የምግብ ደህንነት እና ጤና ለመሳሰሉ ጉዳዮች እንዴት አድርገው ተጠቀሙት ፣አተገባበሩ ምን ይመስል ነበር እና የወሰዷቸው ስትራቴጂዎች የሚያሳይ ገለጻዎች ቀርበዋል፡፡ ትምህርታዊ የሆኑ ዕውቀቶችን ማጋራት እና ጥሩ የሆነ ልምዶች ልውውጥ እየተደረገበት ባለው ወርክሾፕ ላይ አንጎላ፣ ኤርትራ፣ ኢትዮጵያ፣ ጋምቢያ፣ ሌሴቶ፣ ላይቤሪያ ፣ሞዛምቢክ፣ ሩዋንዳ፣ ኡጋንዳ፣ ሳኦቶሚ እና ፕሪንስፒ፣ ሲራሊዮን፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን ፣ሱዳን፣ ታንዛኒያ፣ የመን እና ዛምቢያ ቀርበው ልምዳቸውን ያካፈሉ ሀገራት ናቸው፡፡
የአለም አቀፍ የአከባቢ ፋሲሊቲ (GEF) የብዝሃ ህይወት መጥፋትን፣ የአየር ንብረት ለውጥን፣ ብክለትን እና በመሬት እና በውቅያኖስ ጤና ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን ለመጋፈጥ የሚደረግ የገንዘብ ድጋፍ ነው። 
በአውደ ጥናቱ መገኘት ያልቻሉት የአለም አቀፍ የአከባቢ ፋሲሊቲ (GEF) ሊቀመንበር ካርሎስ ማኑኤል ሮድሪገዝ ፤የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለዉጥ ማዕቀፍ ስምምነት (UNFCCC) ዳይሬክተር እና ፕሮግራም አስተባባሪ ዳንኤል ቫይኦሌቲ ካሉበት ሆነው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡


በአውደ ጥናቱ መጀመሪያ ቀን የአለም አቀፍ የአከባቢ ፋሲሊቲ (GEF) ቴክኒካል ቡድን ስለ ፅህፈት ቤቱ ያቀዳቸው ስራዎች ከነመለኪያዎቻቸው ፤ ከ2022-2026 ስለተቀመጠው ስትራቴጂ አጠቃላይ ወቅታዊ አቋም ፤የገንዘብና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ፤በአረንጓዴ የአየር ንብረት ድጋፍ (GCF) እና የአለም አቀፍ የአከባቢ ፋሲሊቲ (GEF) መካከል የጋራ ፕሮግራም ግንዛቤን እና ልምድ ቀርቧል::

recent News
  • Image Here

    የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ለመቋቋም ያለመ አህጉር …

    04 April 2026
  • Image Here

    04 April 2026
  • Image Here

    የኢትዮ- ሳውዲ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ፎረም በአዲስ አበባ …

    04 April 2026