Image Here

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ(ዶ/ር) እና የግሎባል ግሪን ግሮውዝ ኢኒስቲትዩት የኢትዮጵያ ተወካይ ዳንኤል ኦግቦናያ የሁለቱን ተቋማት እስትራቴጂካዊ ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያዩ

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ(ዶ/ር) እና የግሎባል ግሪን ግሮውዝ ኢኒስቲትዩት የኢትዮጵያ ተወካይ ዳንኤል ኦግቦናያ የሁለቱን ተቋማት እስትራቴጂካዊ ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያዩ

**********************************

አዲስ አበባ ሐምሌ 12/2015 (የፕ.ል.ሚ)

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ(ዶ/ር) እና የግሎባል ግሪን ግሮውዝ ኢኒስቲትዩት የኢትዮጵያ ተወካይ ዳንኤል ኦግቦናያ የሁለቱን ተቋማት እስትራቴጂካዊ ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።

ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የፖለቲካ ቁርጠኝነት በመውሰድ ተጨባጭ እርምጃዎች እየወሰደች እንደምትገኝ ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

ከአገር አቀፍ ፖሊሲዎች፣ስትራቴጂዎች እና እቅዶች ጋር በተጣጣመ መልኩ የአረንጓዴ አሻራን ጨምሮ ሌሎች መርሐ-ግብሮችን በመቅረጽ እየተገበረ ይገኛል ብለዋል።

በአረንጓዴ አሻራ ከጉባኤዎች እና አውደ ጥናቶች ያለፈ መልክዐ ምድርን ዳግም ወደነበረበት በመመለስ እና የዜጎችን ኑሮ በማሻሻል ረገድ ተጨባጭ ውጤቶች መገኘታቸውን አመልክተዋል።

ኢኒስቲትዩቱ የመንግስት ፍላጎቶች እና የትኩረት አቅጣጫዎች በሆኑ ጉዳዮች ላይ ተቋማዊ የአቅም ግንባታ ድጋፍ እንዲያደርግም ነው ሚኒስትር ፍጹም ጥሪ ያቀረቡት።

የግሎባል ግሪን ግሮውዝ ኢኒስቲትዩት የኢትዮጵያ ተወካይ ዳንኤል ኦግቦናያ በበኩላቸው ተቋሙ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር የአየር ንብረት ለውጥ ለመከላከል የተሰጠውን ኃላፊነት በተደራጀ መልኩ መደገፉን እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ በነሐሴ/2015 በሚካሄደው የአፍሪካ የሚኒስትሮች የአካባቢ ጉዳይ ጉባኤ፣የአፍሪካ የአየር ንብረት ሳምንት፣ በተባበሩር አረብ ኤምሬቶች በሚካሄደው 28 ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 28) ለሚደረጉ ቅድመ ስብስባዎች እና ሌሎች ቁልፍ ሁነቶች ላይ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር በትብብር መስራት እንደሚፈልግ አመልክተዋል።

ከውይይቱ በኋላ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር የግሎባል ግሪን ግሮውዝ ኢኒስቲትዩት የአምስት ዓመት አገር አቀፍ የእቅድ ማዕቀፍ(ከእ.አ.አ 2023 እስከ 2027) አፅድቋል።

በማዕቀፉ አማካኝነት ኢኒስቲትዩቱ ሁሉን አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ስትራቴጂ የሆነውን የኢትዮጵያ የረዥም ጊዜ ዝቅተኛ የካርቦን ልቀት ልማት ስትራቴጂ ላይ ትኩረት ያደረገ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቦለታል።

መንግስት እ.ኤ.አ እስከ 2050 በኢትዮጵያ የካርበን ልቀት ዜሮ ለማድረስና በዓመት ከ865 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር የሚያስችል የረዥም ጊዜ ዝቅተኛ የካርበን ልቀት ስትራቴጂ በግንቦት/2015 ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ነው።

recent News
  • Image Here

    የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ(ዶ/ር) እና የግሎባል ግሪን …

    04 April 2026
  • Image Here

    04 April 2026
  • Image Here

    04 April 2026