Image Here

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር  ሰራተኞችና አመራር አካላት  የበጎነት ቀንን አከበሩ፡፡


******************************************************************************
ጳጉሜ 3/2015 አዲስ አበባ (የፕ.ል.ሚ)
የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሰራተኞችና አመራር አካላት  የበጎነት ቀንን ለማሰብ የመቄዶንያ መስራች  የክብር ዶክተር ቢኒያም በለጠን በመጋበዝ  ዕለቱን አክብረዋል፡፡ 
መቄዶንያ የበጎነት ተምሳሌት ከመሆኑም በላይ በስሩ በርካታ ዜጎችን አቅፎ የያዘ የመንግስትን፤ የሴክተሮችንና የማህበረሰብን ሃላፊነት ጨምሮ እየሰራ  የሚገኝ ተቋም ነው ያሉት  የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶክተር ፍፁም አሰፋ የበጎነት ቀን ስናከብር በዙሪያችን የሚገኙትን አቅመ ደካማ እና ታማሚ ወገኖቻችን በመርዳት መሆን እንዳለበት ገልፀዋል።  በጎ ምግባር በአንድ ቀን ብቻ ተወስኖ የሚውል ሳይሆን በለት ተለት እንቅስቃሴያችን ውስጥ ሊኖር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ወደ አዲሱ ዓመት ስንሽጋገር ጳጉሜ የተለች የኢትዮጲያውያን ወር በመሆኗ ቀናቶቹን እንደ ሀገር ትልቅ ዋጋ ያላቸው ጉዳዮችን አንስተን በነዚህ ቀናት ሰይመናል ብለዋል ክብርት ሚኒስትር ፡፡ የበጎነት ቀን በተለየ ከዚ በፊት ባከበርናቸው የጳጉሜ ቀናት ውስጥ የነበረ ሲሆን ይሄ ድርጊት በየግዜው በሰዎች ውስጥ እንዲቀርና በጎ ተግባት ላይ እንዲውሉ ታስቦ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ክብርት ወ/ሮ ጥሩማር አባተ በበኩላቸው የበጎነት ቀንን ስናከበር የመቄዶኒያ መስራችና ባለቤት የክብር ዶክትር ቢኒያም በለጠን ጋብዘን በመሆኑ ትክክለኛ ውስኔ ነው ያሉ ሲሆን ከመቄዶኒያ በተጨማሪ ሌሎች ድጋፎችን ሚኒስቴሩ እያደረገ እና ለማድረግም እያቀደ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የበጎነትን ቀን ስናከበር እንደ ሀገር ከችግር ልንወጣ የምንችለው ስንተባበር ስንተጋገዝ ስለሆነ እንደ መቄዶንያ ላሉ ተቋማት በምንችለው አቅም በዕውቀትም፤ በጉልበትም፤ በገንዘብም እንዲሁም በመጎብኘት ጭምር አለንላቹ ልንል እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያ በተለይም በአሁኑ ወቅት ተፈጥሯዊም ሆነ ሰው ሰራሽ ችግሮችን እየተጋፈጠች በመሆኑ መተባበር እና መተጋገዝ ቅድሚያ የሚሰጣቸው መፍትሔዎች መሆናቸውን ልብ ልንል እንደሚገባ አንስተው የበጎነት ቀንን ስናከበር አቅመ ደካማ ወገኖቻችን በማሰብ መሆን አንዳለበት ገልፀዋል፡፡
የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አማካሪና የፅ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ሻሎም ገ/ድንግል በጎነት በአንድ ቀን አውርተን ወይም አድርገን የምንጨርሰው ጉዳይ አይደለም ነገር ግን አንድ ቀን አመቻችቶ ስለ በጎነት ጉዳይ መወያየታችን ደግሞ የተሻለ እንድናደርግ እና እንድናግዝ ያደርገናል ያሉ ሲሆን መቄዶኒያ እየሰራ ያለው ስራ ትልቅ  በመሆኑ ተደራሽነቱን በማስፋት ወደ ክልሎች የሚያድግበትን ሁኔታ መፍጠር የኛ ሃላፊነት ስለሆነ አሻራችንን ማሳረፍ ይኖርብናል ብለዋል፡፡እስካሁን ምናደርው ድጋፍ በርቀት የነበረ ሲሆን ከአሁን በኃላ ግን በቅርበት በመሄድ እና በመጎብኘት ልንስራቸው ምንችላቸውን ነገሮች በመረዳት የተቻለንን የምናደርግ ይሆናል ሲሉ አብራርተዋል፡፡
በዕለቱ የተገኙት የመቄዶንያ መስራች የክቡር ዶክተር ቢኒያም በለጠ በበኩላቸው ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር የቤተሰብ ግንኙነት ነው ያለን ያሉ ሲሆን ለሚያስፈልገን ነገር ሁሉ ለሚደረገው ድጋፍ ምስጋና አቀርባለሁ፡፡
ሰውን ለመርዳት ሁሉም ሰው እንደሚችል አምናለው ምክንያቱም ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ በመሆኑ ነው ስለዚህ ሁሉም እዚህ ያለው የተቋሙ ሰራተኛ ይሄንን ማድረግ ይችላል ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ የጳጉሜ ቀናት በፕላንና ልማት ሚንስቴር በተለያዩ ዝግጅቶች በመከበር ላይ ናቸው።

recent News
  • Image Here

    የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሰራተኞችና አመራር አካላት የበጎነት ቀንን …

    04 April 2026
  • Image Here

    04 April 2026
  • Image Here

    የኢትዮጵያ የሥነ-ህዝብና ጤና ጥናት መረጃ የማሰባሰብ ሂደት በስኬት …

    04 April 2026