Image Here

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ከፍተኛ አመራሮች ከዓለም ባንክ የፕሮግራሞች ገለልተኛ ግምገማ ቡድን ጋር ተወያዩ፡፡


አዲስ አበባ ሰኔ 24/2015 ዓ.ም የፕ.ል.ሚ

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ከፍተኛ አመራሮች ከዓለም ባንክ የፕሮግራሞች ገለልተኛ ግምገማ ቡድን ጋር ተወያዩ፡፡
ገለልተኛ ቡድኑ የባንኩን ከ2012-2022 በኢትዮጵያ የነበረዉን ተሳትፎ ለመገምገም የመጣ ሲሆን ከተለያዩ ዘርፎች ጋር እንደሚገናኝም ይጠበቃል፡፡
ከግምገማዉ በኋላም ቀጣይ እቅዶችን በማዘጋጄት የልማት ትብብር መስኮችን ይለያል ፡፡


ግምገማዉ ባንኩ በኢትዮጵያ የሰራቸዉ የልማት ትብብር ስራዎች ከሚመለከታቸዉ የመንግስት አካላት ጋር በመሆን በዝርዝር የሚገመግም ሲሆን ለአብነትም የአየር ንብረት ለዉጥ ጋር የተገናኙ ተግባራት እንዲሁም የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ ረገድ የተሰሩ ስራዎችም ይጠቀሳሉ፡፡
ባንኩ በኢትዮጵያ ያለዉን የልማት ትብብር ተሳትፎ በተመለከተ ከፕላንና ልማት ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ፍጹም አሰፋ እንዲሁም ሚኒስትር ዲኤታዉ ክቡር ዶ/ር ነመራ ገበየሁ ጋር ሰፈ ዉይይት አድርገዋል፡፡ከግምገማዉ ቀጥሎ በሚዘጋጁ እቅዶች ላይ ባንኩ የኢትዮጵያን የልማት የትኩረት መስኮችና ቅድሚ የሚሰጣቸዉን ፍላጎቶች በመለዬት የትብብር ማዕቀፉ እንደሚዘጋጅ ይጠበቃል፡፡
የባንኩ የፕሮግራሞች የግምገማ ቡድን አባላት ከተለያዩ አካላት ጋር በመገናኜት የሚወያዩ ሲሆን ካለፉት አስር ዓመታት ተሞክሮዎችን በመዉሰድና የቀጣይ የኢትዮጵያ የልማት መስኮች በማገናዘብ አዲስ የልማት ትብብር ማዕቀፍ ይቀርጻል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

recent News
  • Image Here

    የፕላንና ልማት ሚኒስትር ከፍተኛ አመራሮች ከዓለም ባንክ የፕሮግራሞች …

    04 April 2026
  • Image Here

    04 April 2026
  • Image Here

    04 April 2026