Image Here

የአዉሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የሚያደርገዉን የልማት ትብብር እንደሚያጠናክር ገለጸ


ሰኔ 22/2015 ዓ.ም ፣ የፕ.ል.ሚ (አዲስ አበባ)
የአዉሮፓ ህብረት የልማት ትብብር በኢትዮጵያ የሚያደርጋቸዉን የልማት ትብብሮች አጠናክሮ እንደሚቀጥል የህብረቱ የልማት ትብብር ሃላፊ ዶ/ር ስቴፋን ሎክ አስታወቁ፡፡
የፕላንና ልማት ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ፍጹም አሰፋ ሃላፊዉን በጽህፈት ቤታቸዉ ተቀብለዉ አነጋግረዋል፡፡


የአዉሮፓ ህብረት የልማት ትብብር በኢትዮጵያ ለረዥም ጊዜያትን ያስቆጠረ የልማት ትብብሮች ሲያደርግ ቆይቷል። የሰሜኑን ጦርነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ከስምምነት በመደረሱና ስምምነቱን ለማጽናት እተሰሩ ያሉ ስራዎች ፍሬያማ መሆናቸዉን ተከትሎ  ደግሞ የአዉሮፓ ህብረት ትብብሩን ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚፈልግ ነዉ የትብብሩ ሃላፊ ዶ/ር ስቴፋን ሎክ ከፕላንና ልማት ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ፍጹም አሰፋ ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ያረጋገጡት፡፡


ህብረቱ የመካከለኛ ዘመን የልማት ትብብር ማዕቀፍ አዘጋጅቶ እያጠናቀቀ መሆኑን ያነሱት ሃላፊዉ በህብረቱ ቅድሚያ ትኩረት ተብለዉ የተለዩ ጉዳዮች ከኢትዮጵያ ፍላጎት ጋር  የተናበቡ እንዲሆኑ እንፈልጋለን ብለዋል፡፡የፕላንና ልማት ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ፍጹም አሰፋ በበኩላቸዉ መንግስት የመካከለኛ ዘመን የልማትና ኢንቨስትመንት እቅድና የሃገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ሁለተን በተመለከተ በዝርዝር አብራርተዉላቸዋል፡፡በተለይም መንግስት ቅድሚያ የሚሰጣቸዉን የልማት ፍላጎቶችና የህዝብን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አንጻር የሚጠበቁ ትብብሮችን በተመለከተ ከህብረቱ የልማት ትብብር የመካከለኛ ዘመን እቅድ ጋር የተናበበ አድርጎ ለመሄድ በቀጣይም በቴክኒክ ደረጃ ዉይይቶች እንደሚደረጉ አንስተዋል፡፡

recent News
  • Image Here

    የአዉሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የሚያደርገዉን የልማት ትብብር እንደሚያጠናክር ገለጸ

    04 April 2026
  • Image Here

    የፕላንና ልማት ሚኒስትር ከፍተኛ አመራሮች ከዓለም ባንክ የፕሮግራሞች …

    04 April 2026
  • Image Here

    04 April 2026