የፕላንና ልማት ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ፍጹም አሰፋ የፈረንሳይ ንግድ ምክር ቤት አባላትን በጽህፈት ቤታቸዉ አነጋገሩ፡፡

ክብርት ሚኒስትር ለልዑካን ቡድኑ አባላት የሃገር በቀል ኢኮኖሚክ ሪፎርም ሁለትን ይዘትና ዝግጅት በተመለከተ ገለጻ አድርገዉላቸዋል ፡፡በተለይም መንግስት የግሉን ዘርፍ የኢኮኖሚ ተሳትፎ ለማሳደግ በሪፎርሙ ያስቀመጣቸዉን ቁልፍ ሃሳቦችን ያብራሩት ክብርት ሚኒስትር የፈረንሳይ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ለሚያደርጉት የኢንቨስትመንት ተሳትፎ አመስግነዋል፡፡የፈረንሳይ ንግድ ምክር ቤት ልዑካን ቡድን አባላት በበኩላቸዉ በርካታ የፈረንሳይ ባለሃብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች በመሳተፍ ላይ መሆናቸዉን ገልጸዉ በቀታይም ተሳትፎአቸዉን ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላቸዉ አረጋግጠዋል፡፡
ሰኔ 20 /2015 ዓ.ም የፕ.ል.ሚ(አዲስ አበባ)