Image Here

የፕላንና ልማት ሚኒሰቴር የ2015 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ እና የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሰራተኞችና አመራር አካላት ጋር ተወያዩ፡፡

የፕላንና ልማት ሚኒሰቴር የ2015 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ እና የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሰራተኞችና አመራር አካላት ጋር ተወያዩ፡፡

********************************************

ነሐሴ 27 አዳማ (የፕ.ል.ሚ)

የፕላንና ልማት ሚኒሰቴር የ2015 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ እና የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሰራተኞችና አመራር አካላት በአዳማ ከተማ ተወያዩ፡፡

በውይይት መድረኩ የ2015 በጀት ዓመት ሪፖርት በስትራቴጂክ ጉዳዮች ክፍል ስራ አስፈጻሚ አቶ አስራት ተረዳ የ2015 በጀት ዓመት የፕላን ልማት ሚኒስቴር የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በስትራቴጂክ ግቦች ማለትም ተቋማዊ የማስፈጸም አቅም፣ የሀብት አጠቃቀምና የአገልግሎት አሰጣጥ አሰራር ማጎልበት፣ በልማት ዕቅድ ጥራ ያለው የኢኮኖሚ እድገት እና የጋራ ብልፅግና ማረጋገጥ (አንድ ዕቅድ አንዱ ሪፖርት) የኢኮኖሚ ትንተና ሞዴሊንግ እና ትንበያ አቅም መገንባት፣ እና የኢኮኖሚ አካውንትና ስታትስቲክስ መረጃዎችን ማመንጨት የዲጂታል የልመት ዕቅድ ክትትልና ግምገማ ስርዓትን መዘርጋትና ማዘመን እና አፈፃፀም ሂደት ያጋጠሙ ችግሮች እና የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎች እንዲሁም የ 2016 ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ ገለፃ አድርገዋል፡፡

ሌላው የውይይት አጀንዳ የነበረው የመካከለኛው ዘመን የልማትና የኢንቨስትመንት ዕቅድ አጠቃላይ እይታ እንዲሆን የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ በአየር ንብረት ለውጥ የመረጃ አሰባሰብ እና የአንድ ዕቅድ አንድ ሪፖርት ስርዓት እና የዕቅዱ ማስፈፀሚያ ፕሮግራሞችና ንዑስ ፕሮግራሞች ላይ እስከታች ሰራተኛ ድረስ ወርዶ የሚሰራበት ሂደት ላይ ያተኮረ ነበረ፡፡

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ክብርት ዶክተር ፍፁም አሰፋ ይህ አይነቱ ውይይት ይጠቅማል ያሉ ሲሆን ምን ፈፅመናል ምንስ ለመፈፀም አስበናል ምንስ ይዞታ ላይ ነው ያለው እንደ ተቋም ሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮችንም የምናነሳበት መድረክ በመሆኑ ነው፡፡ እንደተቋም 2015 ምን ነበረ የተፈፀመው የጎደለውስ ምን ነበር ምክንያቱስ እንዲሁም በ2016 ዓ.ም. ለቀጣይ ሶስት አመታት ምን ለመፈፀም ታቅዷል የሚለውን ለማሳየት ሲሆን እንደ ኃላፊም ምን እንፈፅም የሚለውን ከሰራተኛ ጋር ለመነጋገር ምቹ መድረክ ነው፡፡

 

የውይይቱ ተሳታፊዎች ከሰራተኛ ምደባ፤ ከካፒታል በጀት፤ ሰውኃብት ስልጠና የትምህርት ዕድል የህፃናት ማቆያ፤ ሰራተኛ ድጎማ፤ ከኃብት ምዝገባ፤ የሰራተኛ ፍልሰት እና ሴቶችን ከማብቃት ጋር ተያይዞ ያላቸዉን ሀሳብና አስተያየት ሪፖርቱን ላቀረቡ ስራ አስፈፃሚዎች እና ሃላፊዎች አቅርበዉ ምላሽና አስተያየት ተሰቶባቸዋል።

የሚኒስትር መስሪያ ቤት የፅህፈት ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ሻሎም የቀረበዉ ሪፖርት የየክፍሉ የስራ አፈፃፀም እንደሚወክልና ከሴቶችን ማካተት ጋርም ተያይዞ የተነሳዉ ሀሳብ ትክክለኛ በመሆኑ እንደ ግብዓት የምንወስደዉ ነዉ ብለዋል።የማህበራዊ ጉዳይ ኮሚቴ በተሻለ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ጠቁመዋል።

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ሚኒስቴር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ጥሩማር አባተ የተነሱት ብዙዎቹ ሀሳቦች እንደ ግብዓት የምንወስዳቸዉ እንደ ተቋም በ2015 በጀት ዓመት ትልልቅ ሀገራዊ ጉዳዮች እንደተሰሩና ለዚህም ዉጤት በተቋሙ ያላችሁ ሠራተኞች ሚና የማይዘነጋ ነዉ ብለዋል።

በመድረኩ የተነሳዉ ሀሳብ አስተያየትና ጥያቄ እንደ ሀገርም እንደ ተቋምም ከተሰጠን ተልዕኮ አንፃር ዉጤታማ ለመሆን ተፅዕኖ ስለሚያሳድር መመለስ ያለባቸዉ እንደሆኑ አሳስበዉ የሰራተኛ ፍልሰትና የኑሮ ሁኔታ እንደ ሀገር እየተሰራበት ያለ ጉዳይ በመሆኑ በቅርብ ይፈታሉ ብለዉል።ያለን ዉስን በጀትና የሰዉ ሀብት ሳይገድበን የተሰጠንን ተልዕኮ እያስፈፀምን ስላለን እድለኛ ነን ያሉት የፖላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶክተር ነመራ ገበየዉ የታቀደዉን ለመከታተል እና ከማቀድም ጋር የተወሰኑ ክፍተቶች እንዳሉ ይታወቃል ለዚህም የዴስክ ሃላፊዎች ባለሞያዎችን ከማሰራትና ምሳሌ ከመሆን አንፃር ትልቅ ሃላፊነት እንዳለባቸዉ ጠቁመዋል።የዚህ አይነት መድረክ በየሩብ ዓመቱ ሊኖር እንደሚችል ጠቁመዋል።

የውይይቱ መዝጊያ ላይ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ክብርት ዶክተር ፍፁም አሰፋ በቀጣይ 3 በጀት ዓመት እንደ ዕቅድ ሁሉም ባለሞያ ባለበት የስራ ሃላፊነት ስራዎችን ቆጥሮ ተረክቦ የሚሰራበትንና ያልሰራ የሚጠየቅበትና ለሰራ ደግሞ የሚበረታታበትን አሰራር የሚዘረጋ ይኖራል ያሉት ሚኒስትሯ ተቋሙ እንደ ሀገር የሚጠበቅበትን እያደረገ መሆኑ የየዘርፉ ባለሞያዎች ሃላፊነታቸዉ ባይወጡ ለዚ ዉጤት እንደማይደረስ ማወቅ እንደሚቻል ገልፀዋል።በቀጣይ የተጀመረዉ የተለያዮ የፍጆታ ዕቃዎች ለሰራተኛ በአነስተኛ ዋጋ ማቅረብ እና የካፌ አገልግሎትን ለማሻሻል እንደሚሰራና ከህፃናት ማቆያ ግንባታ ጋር ተያይዞ ከUNICEF ጋር በመነጋገር አስፈላጊዉን ቁሳቁስ እንደሚያሟሉ በገቡት ቃል መሰረት ባለዉ የተጣበበ ክፍል ለመስራት እንደታሰበ ገልፀዉ መጪዉ አዲስ ዓመት የሰላም እንዲሆን ተመኝተዋል ።

recent News
  • Image Here

    የፕላንና ልማት ሚኒሰቴር የ2015 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም …

    04 April 2026
  • Image Here

    19ኛው የአፍሪካ የአካባቢ ሚኒስትሮች መደበኛ ጉባኤ አዲስ አበባ …

    04 April 2026
  • Image Here

    Ethiopia Shared Its Experience on How the Country …

    04 April 2026