Image Here

ኢትዮጵያ በ20ኛው የዓለም አቀፍ የሥራ ድርጅት አህጉራዊ ጉባኤ ላይ ሁሉን ያሳተፈ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ እየተከተለች ያለውን ስትራቴጂ አቀረበች፡፡

ኢትዮጵያ በ20ኛው የዓለም አቀፍ የሥራ ድርጅት አህጉራዊ ጉባኤ ላይ ሁሉን ያሳተፈ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ እየተከተለች ያለውን ስትራቴጂ አቀረበች፡፡

**********************************************************************************************************************

አዲስ አበባ | ግንቦት 11/2017 ዓ.ም

የኢፌዴሪ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ፍጹም አሰፋ "በ20ኛው የአለም አቀፍ የሥራ ድርጅት የሥራ ላይ ተኮር ባለሙያዎች አህጉራዊ ጉባኤ" ላይ ኢትዮጵያ ሁሉን ያሳተፈ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ እየተከተለች ያለውን ስትራቴጂ በዝርዝር አቀረቡ።

ክብርት ዶ/ር ፍጹም ኢትዮጵያ የስራ ዕድል ፈጠራን፣ ክህሎት ማሳደግንና ስራ አጥነትን በመቅረፍ ላይ ትኩረት ያደረገ የ10-ዓመት የልማት እቅድ በመተግበር ላይ መሆኗን ገልፀዋል። በተለይም የኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ፣ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት እንዲሁም የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ላይ እየተደረጉ ያሉ ማሻሻያዎች የስራ ዕድሎችን በመፍጠርና እንደ ወጣቶች ስራ አጥነትና የክህሎት አለመዛመድ ያሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ወሳኝ ሚና እየተጫወቱ መሆናቸውን አስረድተዋል።

recent News
  • Image Here

    ለአየር ንብረት የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ (CRGE) ፎረም ኢትዮጵያ …

    04 April 2026
  • Image Here

    ኢትዮጵያ በ20ኛው የዓለም አቀፍ የሥራ ድርጅት አህጉራዊ ጉባኤ …

    04 April 2026
  • Image Here

    በኢትዮጵያ ሶስተኛው የሀገር አቀፍ በፈቃደኝነት ግምገማ (VNR) 2025 …

    04 April 2026