Image Here

የኘላንና ልማት ሚኒስቴር በነፃነትና በገለልተኝነት ለህብረተሰቡ ብቃት ያለው አገልግሎት ለመስጠት በሚያስችለው የሲቪል ሰርቪስ የሪፎርም ስራን ወደ ተግባር ለመለወጥ የአመራሩና የሰራተኛው ሚና ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ። መጋቢት 18/2017 ዓ.ም (ፕ.ል.ሚ - አዲስ አበባ)

የኘላንና ልማት ሚኒስቴር በሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ስራዎች ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የኘላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አቶ ስዪም መኮንን እንደተናገሩት ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣንና ተግባር መሰረት ነፃና ገለልተኛ ተቋም በመገንባት ለህብረተሰቡ ብቃት ያለው አገልግሎት መስጠት ይጠበቅበታል።

በዚሁ መሰረት በፌዴራል ደረጃ በስምንት ሚኒስቴር ተቋማት በተጀመረው የሪፎርም ስራ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር አንዱ መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትር ዲኤታው በሪፎርሙ መሰረት በተዘጋጀው ተቋማዊ የለውጥ ክፍተት ልየታ ዳሰሳ ጥናት እና በተቋማዊ ሪፎርም ፍኖተ ካርታ ሰነድ ላይ የሚኒስትሩ አመራሮችና ሰራተኞች በተቀመጡ የአገልግሎት ማሻሻያዎችና የመፍትሄ እርምጃዎች ሀሳብ በመስጠትና በማዳበር ወደ ተግባር ለመለወጥ በሚደረገው እንቅስቃሴ በባለቤትነት ድርሻቸውን ሊያበረክቱ እንደሚገባ አስረድተዋል።

ክቡር አቶ ስዩም አክለውም የሀገራዊ ለውጥ አካል የሆነውንና ለዘመናት የቆየውን የተቋም ግንባታ ስብራቶችን በመጠገን ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማምጣት ሪፎርሙ የላቀ ጠቀሜታ እንዳለውና በቀረበው የመነሻ ሰነድ የአፈፃፀም አቅጣጫዎች ስልቶችና የተቀመጡ ሲሆን ለስኬታማነቱ አስፈላጊውን ግብአት በመስጠት ረገድ ሚናቸውን እንዲወጡ የተዘጋጁትን የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረኮችን በንቃት በመሳተፍ ሚናቸውን እንዲወጡ አሳሰበዋል።

በግንዛቤ መፍጠሪያ መድረኩ በተቋሙ ባሉ ሁሉኑም የስራ ክፍሎች ያካተተ ተቋማዊ ለውጥ ክፍተት ልየታ፣ ከክፍተቱ በመነሳት የቀጣይ የተቋማዊ ሪፎርም ፍኖተ ካርታ እንዲሁም ስለ ሪፎርሙ አጠቃላይ መነሻና አሰራር የተመለከተ የመነሻ ፅሁፎች ቀርበዋል። የሚኒስትሩ አመራሮችና ሰራተኞችም ከቀረበው የመወያያ ሰነድ በመነሳት ልዩ ልዩ ሃሳቦችንና አስተያየቶችን በማንሳት ውይይት አካሂደዋል።

recent News
  • Image Here

    የኘላንና ልማት ሚኒስቴር በነፃነትና በገለልተኝነት ለህብረተሰቡ ብቃት ያለው …

    04 April 2026
  • Image Here

    04 April 2026
  • Image Here

    04 April 2026